Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ማህበራዊ ሚዲያዎች የወጣቶች ቀዳሚ የዜና ምንጭ ሆነዋል

0 971

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ማህበራዊ ሚዲያዎች የወጣቶች ቀዳሚ የዜና ምንጭ ሆነዋል

ማህበራዊ ሚዲያዎች የወጣቶች ቀዳሚ የዜና ምንጭ ሆነዋል

ማህበራዊ ሚዲያዎች ለወጣቶች የዜና ምንጭ በመሆኑ ቀዳሚነቱን ከቴሌቪዥን ቀምተዋል።

ከ18 እስከ 24 ዓመት የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ወጣቶችን ያሳተፈ አንድ ጥናት ውጤት እንደሚያመለክተው፥ 28 በመቶዎቹ ወጣቶች ማህበራዊ ሚዲያዎችን እንደ ዋነኛ የዜና ምንጭነት እየተጠቀሙ ነው።

ዜናን ለመከታተል ወደ ቴሌቪዥን እንሄዳለን ያሉት 24 በመቶዎቹ ናቸው።

የሬውተርስ የጋዜጠኝነት ጥናት ኢንስቲትዩት ያካሄደው ይህ ጥናት እንደሚጠቁመው፥ የማህበራዊ ሚዲያን ከሚጠቀሙ ሰዎች መካከል 51 በመቶዎቹ ዜናን ለመከታተል እንደሚገለገሉባቸው ነው የተናገሩት።

በ25 አገራት የሚገኙ 50 ሺህ ሰዎችን ያሳተፈው ይህ ጥናት፥ በተለይም የሞባይል ስልክ ተጠቃሚነት እየሰፋ መምጣት ቀደም ሲል ከተለመዱት የዜና ምንጮች ይልቅ ሰዎች ወደ ማህበራዊ ሚዲያዎች እንዲያዘነብሉ ማድረጉን ጠቁሟል።

ቀዳሚ ተብለው ከተዘረዘሩት ለዜና ምንጭነት ከሚያገለግሉት የማህበራዊ ሚዲያዎች ውስጥ ቀዳሚ የሆነው ፌስ ቡክ ሲሆን፥ ፌስቡክን ከሚጠቀሙ ሰዎች ውስጥም 44 በመቶዎቹ ዜናን ፍለጋ ወደ ማህብራዊ ትስስር መድረኩ እንደሚሄዱ ነው የተመለከተው።

ዩትዩብ፣ ትዊተር እና ዋትስአፕ እንደቅደም ተከተላቸው ቀዳሚ የዜና ምንጭ ሆነው እያገለገሉ ነው።

ሬዲዮ እና ቴሌቪዥንን የመሰሉ የመገናኛ ብዙሃን አሁንም ቀዳሚ የዜና አምራች ሆነው የቀጠሉ ሲሆን፥ በተለይም ጠንከር ላሉ ዜናዎች ዋነኛ መገኛ ሆነው መቀጠላቸውን ገልጿል።

ወደ ማህብራዊ ሚዲያዎች ዜና ፍለጋ ከሚሄዱት ሰዎች መካከል የሚልቁት ለስለስ ያለ ዜናን የሚመርጡ መሆናቸውም ነው በጥናት ውጤቱ ላይ የተመለከተው።

ጥናቱ በዳሰሰባቸው አገራት የጋዜጦች ሽያጭ እየቀነሰ የመጣ ቢሆንም፥ የሰዎች በኦንላይን ዜናን ገዝቶ የማንበብ ፍላጎት ግን አሁንም ዝቅተኛ ነው ብሏል።

 

ምንጭ፦ ቢቢሲ

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy