Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ለመምህራን የሚሰጡ ልዩ ልዩ ጥቅሞች ይፋ ሆኑ

5 2,248

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ለመምህራን የሚሰጡ ልዩ ልዩ ጥቅሞች ይፋ ሆኑ

 

በአዲስ አበባ በስራ አፈጻጸማቸው ውጤታማ የሆኑ መምህራን ሽልማት ተበረከተላቸው።

ዛሬ በአፍሪካ ህብረት በተካሄደው የሽልማት ስነ ስርአት ላይ፥ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በመንግስት ትምህርት ቤቶች ለሚያስተምሩ 128 መምህራን፣ ተቆጣጣሪዎችና ርዕሳነ መምህራን ዕውቅናና የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

በዚህ የሽልማትና ዕውቅና ፕሮግራም ላይ የተገኙት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፥ መንግስት አቅሙ በፈቀደ መጠን ለመምህራን አስፈላጊውን ጥቅማ ጥቅም እንደሚያሟላ ተናግረዋል።

የዛሬው ሽልማትም የስራ ተነሳሽነት በማሳደግ አቅማቸው ከፍ እንዲያደርጉ ከፍተኛ ሚና አለው ብለዋል።

መንግስት ለመምህራን የሚተገብራቸው ማሻሻያዎች ይፋ ያደረጉት የኢፌዴሪ የትምህርት ሚኒስትር አቶ ሽፈራው ሽጉጤ በበኩላቸው፥ መምህራን እስከዛሬ ሲያነሱ የነበሩትን ቅሬታን የፈታ ጥያቄ ተመልሷል ነው ያሉት።

በሃገሪቱ የመምህራንን ተጠቃሚነት በማሳደግ የትምህርት ጥራትን አሁን ካለበት ከፍ ወዳለ ደረጃ ያሸጋግራል ብሎ መንግስት እየተገበራቸው እና የሚተገብራቸውን ማሻሻያዎችንም ይፋ አድርገዋል።

ሚኒስትሩ እንደገለፁት፥ ቀደም ሲል ከሁለት እርከን ይጀምር የነበረው የመምህራን ደሞዝ ከሀምሌ 1 ቀን 2008 ዓመተ ምህረት ጀምሮ በ10 እርከን የሚጀመር ይሆናል።

የእስከዛሬው የመምህራን ደሞዝ ጣሪያ፥ አንድ መምህር በዜሮ አመት የስራ ልምድ ሲቀጠር ከመጀመሪያ ዲግሪ የመነሻ ደሞዝ በሁለት እርከን ከፍ ያለ ነበር።

አሁን በተደረገው ማሻሻያ መሰረት የጀማሪ መምህራን ደሞዝ ከዚህ በፊት ከነበረው የመንግስት የመነሻ ደሞዝ፥ አጠቃላይ በ10 እርከን ከፍ እንዲል ተደርጓል።

ከዚህ በተጨማሪም በስራ አፈጻጸማቸው መምህራን ያገኙት የነበረው የእርከን እድገትም እንዲሻሻል ተደርጓል።

በዚህም መሰረት ከዚህ ቀደም አንድ መምህር በስራ ውጤታማነቱ ከ1 በላይ እርከን ማግኘት አይችልም ነበር።

አሁን የተደረገው ማሻሻያ ግን እንደ ስራ አፈጻጸሙ አንድ መምህር/ት በአንድ ጊዜ እስከ ሶስት እርከን ማደግ የሚችሉበትን አግባብ ይተገብራል።

ከደሞዝ ማሻሻያው በተጨማሪ በአዲስ አበባ ለሚገኙ መምህራን 5 ሺህ የመኖሪያ ቤቶች መገንባታቸውን አንስተዋል።

ሌሎች 19 ሺህ የመኖሪያ ቤቶችም ለአዲስ አበባ መምህራን በመገንባት ላይ መሆናቸውንም ነው የጠቆሙት።

በሌሎች አካባቢዎች እና በተለይም በገጠር አካባቢዎች የሚያስተምሩ መምህራን ደግሞ የመኖሪያ ቤት መስሪያ መሬት በቀላሉ እንዲያገኙ እንደሚደረግ ወይም ቤት ተገንብቶ እንዲሰጣቸው ይደረጋል ብለዋል።

በስራ አፈጻጸማቸው ውጤታማ ለሆኑት መምህራን ሽልማት መበርከቱ ለቀጣይ ትውልድን የማነጽ ስራ ትልቅ አቅም እንደሚሆን የገለጸው ደግሞ የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ነው።

ሽልማቱ እንዳስደሰታቸው የገለጹት ተሸላሚ መምህራን በቀጣይ ከዚህ የተሻለ እንደሚሰሩ ቃል ገብተዋል።

“ክብርና ምስጋና ለህዳሴው ትውልድ አናጺ መምህራን” በሚል መሪ ቃል ነው የሽልማት ስነ ስርዓቱ የተካሄደው።

 

FBC

  1. hai truong giang says

    Thank you a lot for sharing this with all of us
    you really recognise what you’re talking approximately!
    Bookmarked. Please also seek advice from my site =).
    We may have a link trade arrangement among us

  2. Good day! I could have sworn I’ve visited
    your blog before but after going through many of the
    posts I realized it’s new to me. Nonetheless,
    I’m definitely happy I stumbled upon it and I’ll be book-marking it and checking back often!

  3. annoncebaise says

    After going over a number of the blog articles on your web page, I seriously like your technique of writing a blog.
    I bookmarked it to my bookmark site list and will be checking back in the near
    future. Please check out my website too and tell me your opinion.

  4. Shoe Lift for short leg says

    Very interesting details you have mentioned, regards for posting.

  5. livesex says

    My family eѵerʏ time say that ӏ am killing my time ere aat net, however I know I am getting knowledge alll tɦеe time by reading
    thes nic articles.

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy