Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ሚኒስቴሩ በአዲስ አበባ የአጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት በሽታ ምልክት በሁሉም ክፍለ ከተሞች መታየቱን ገለፀ

0 1,253

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ሚኒስቴሩ በአዲስ አበባ የአጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት በሽታ ምልክት በሁሉም ክፍለ ከተሞች መታየቱን ገለፀ

ሚኒስቴሩ በአዲስ አበባ የአጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት በሽታ ምልክት በሁሉም ክፍለ ከተሞች መታየቱን ገለፀ

በአሁኑ ወቅት እየጣለ ያለውን ዝናብ ተከትሎ የአጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት በሽታ ምልክት የታየባቸው ህሙማን ከሰኔ 2 2008 ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ መገኘታቸው መገለፁ ይታወሳል።

በአሁኑ ወቅትም በሁሉም ክፍለ ከተማ ከ2 እስከ 15 ህሙማን በመታየታቸውን ያስታወቀው የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር፥ የታማሚዎች ቁጥር መጨመሩን እና እስካሁን ሞት እንዳልተመዘገበም አስታውቋል።

በሽታው እንዳይዛመት የፌደራል ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ከአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ጋር በመሆን ህብረተሰቡን በማሳተፍ አስፈላጊውን የመከላከልና የመቆጣጠር ስራ እየሰራ እንደሚገኝም ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

ይህን ተግባር በአግባቡ ለመፈጸም የሚያስችሉ በኮማንድ ፖስቶች የተዋቀሩ የክትትል ስርዓት በጤና ጥበቃ ሚኒስቴርና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እስከ ወረዳ ተዋቅሮ በየእለቱ ክትትል እያደረገ በመስራት ላይ ነው።

በመሆኑም በአዲስ አበባና አካባቢው የሚገኙ ነዋሪዎች ለዚህ ስራ የተሰማሩ ባለሙያዎችና አካለት በሚሰጡት ምክር መሰረት አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንድታደርጉ የፌደራል ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አሳስቧል።

የአጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት በሽታ ምክንያቶች

የአጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት በሽታ በንጽህና መጓደል በሚከሰቱ በዓይን የማይታዩ የተለያዩ ጥቃቅን ተዋህሲያን አማካኝነት የሚከሰት ሲሆን፥ በተለይም በተበከሉ ምግቦች፣ የመጠጥ ውሃና በሌሎች መተላለፊያ መንገዶች ከሰው ወደ ሰው በከፍተኛ ፍጥነት የሚተላለፍ ነው።

ምልክቶች

ድንገት የሚጀምር መጠነ ብዙ፣ ተከታታይና አጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት የሚከሰት ሲሆን፥ ከዚህም የተነሳ ከሰውነት ጠቃሚ ንጥረ ነገሮችና ፈሳሽ በብዛት ስለሚወገዱ ከፍተኛ የሰውነት ድርቀት (የአይን መሰርጐድ፣ የአፍና የምላስ መድረቅ፣ እንባ አልባ መሆን፣ የሽንት መጠን መቀነስና የቆዳ መሸብሸብ) ያስከትላል።

የመከላከያ መንገዶች፡

በሽታውን በቀላሉ መከላከል የሚቻል ስለሆነ ከበሽታው ራስንና ቤተሰብን ብሎም አካባቢን ለመከላከል የግልና የአካባቢዉን ንጽህና በሚገባ መጠበቅ አስፈላጊ ነው።

የበሽታው ምልክት የታየበት ሰዉ ከተገኘ በአስቸኳይ በአቅራቢያ ወደሚገኝ ጤና ተቋም እንዲሄድና አስፈላጊዉን ምርመራና ህክምና ማግኘት ይኖርበታል።

እንዲሁም፦

• ውሃ አፍልቶና አቀዝቅዞ መጠቀም

• በውሃ ማከሚያ መድሃኒት የታከመ ውሃ መጠቀም

• ምግብን በሚገባ አብስሎ በትኩስነቱ መመገብ

• የምግብ ዕቃዎች ንጽህና መጠበቅ

• መፀዳጃ ቤትን በአግባቡ መጠቀም

• እጅን ከመጸዳጃ ቤት መልስ፣ ምግብ ከማዘጋጀት በፊት፣ ምግብ ከማቅረብ በፊት፣ ምግብ ከመመገብ በፊት፣ ሕጻናትን ካጸዳዱ በኋላ፣ ሕጻናትን ጡት ከማጥባትና ከመመገብ በፊት አንዲሁም ለበሽተኛ እንክብካቤ ካደረጉ በኋላ በሣሙና በሚገባ መታጠብ

• ማናቸውንም ከቤት የሚወጣ ደረቅ ወይም ፈሳሽ ቆሻሻ ውሃን እንዳይበክል በአግባቡ በተመደበለት ስፍራ ማስወገድ

• በዚህ በሽታ የተያዘ ሰው በፍጥነት ወደ ሕክምና ተቋም መውሰድ

• ከበሽተኛው ከሚወጣ ፈሳሽ ጋር ንክኪ ያላቸውን እቃዎችና ቦታዎችን በአግባቡ ማጽዳት

ጠቃሚ መረጃዎች

የበሽታው ምልክት ለታየባቸዉ ሰዎች አፋጣኝ ህክምና ለመስጠት በሁሉም ክፍለ ከተማዎች 14 ማከሚያ ጣቢያዎች የተቋቋሙ ስለሆነ እንደሚከተለው መደሚቀርብ ህክምና ጣቢያ መሄድ ይቻላል፡፡

ጣቢያዎቹም፥

1. አቃቂ ክፍለ ከተማ፦ ስርጢ ጤና ጣቢያ

2. ነፋስ ስልክ ላፈቶ ክፍለ ከተማ፦ ወረዳ 1 ጤና ጣቢያ

3. ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ፦ ሚኪሌላንድ ጤና ጣቢያ

4. ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ፦ ወረዳ 4 ዓለም ባንክ ጤና ጣቢያ

5. የካ ክፍለ ከተማ፦ ወረዳ 12 ጤና ጣቢያ

6. ቂርቆስ ክፍለ ከተማ፦ ቂርቆስ ጤና ጣቢያ

7. ልደታ ክፍለ ከተማ፦ በለጥሻቸው ጤና ጣቢያ

8. አራዳ ክፍለ ከተማ፦ወረዳ 3 ጤና ጣቢያ

9. ጉለሌ ክፍለ ከተማ፦ ሰሜን ገበያ ጤና ጣቢያ

10. ጉለሌ ክፍለ ከተማ፦ አዲሱ ገበያ ጤና ጣቢያ

11. ቦሌ ክፍለ ከተማ፦ ወረዳ 10 (አሞራዉ) ጤና ጣቢያ

 

 

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy