Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

በሺዎች የሚቆጠሩ የኤርትራ ስደተኞች የተ.መ.ድ አቋምን በመደገፍ በእስራኤል ሰልፍ ወጡ

0 580

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

በሺዎች የሚቆጠሩ የኤርትራ ስደተኞች የተ.መ.ድ አቋምን በመደገፍ በእስራኤል ሰልፍ ወጡ

ባለፈው ወር የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በኤርትራ የሚፈፀመውን ሰብአዊነትን የጣሰ ድርጊት አስመልክቶ ያወጣውን ሪፖርት በመደገፍ በእስራኤል የሚገኙ የአገሪቱ ስደተኞች የድጋፍ ሰልፍ ወጥተዋል፡፡

የአገሪቱ መንግስት የገዛ ህዝቡን ያሰቃያል፤ በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ኤርትራዊያንንም እንደ ባሪያ ባልፈቀዱት ስራ ያሰማራል ሲል የመንግስታቱ ድርጅት ሪፖርት ይወቅሳል፡፡

የኤርትራ ባለስልጣናት በበርካታ የአስገድዶ መድፈርና የግድያ ወንጀሎች ተዘፍቀዋል ሲል ሪፖርቱ የገለፀ ሲሆን ባለስልጣናቱ በአለማቀፉ ፍርድቤት እንዲቆሙም ጠይቋል፡፡

የኤርትራ መንግስት ይህንን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሪፖርት ሃሰት ነው ሲል ያጣጣለው ቢሆንም በእስራኤል የሚገኙ ኤርትራዊያን ግን ሪፖቱ ለደረሰባቸው ስቃይ ትክክለኛ ነጸብራቅ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በእስራኤል የአውሮፓ ህብረት ጽሕፈት ቤት ዙሪያ ሪፖርቱን ደግፈው የኤርትራን ባለስልጣናት ወንጀል በሰላማዊ ሰልፍ መስክረዋል፡፡

በዚህ ሁኔታ ውስጥ የእስራኤል መንግስት አብዛኛዎቹን አፍሪካውያን ስደተኞችን ህገወጥ ስራ ፈላጊዎ በሚል ወደ መጡበት እመልሳለሁ ማለቱ ኤርትራውያን ስደተኞችን ስጋት ላይ እንደጣለ ሰልፈኞቹ ገልፀዋል፡፡

የዓለም ስደተኞች ብዛት በታሪክ ከፍተኛ ቁጥር ባስመዘገበበት በአሁኑ ወቅት የኤርትራ ስደተኞች የስደት ስቃዩ ዋነኛ ተጋሪዎች ናቸው፡፡

የኤርትራ ስደተኞች በፖለቲካዊ ችግር ምክንያት ጦርነት ከሌለባት አገራቸው በመንግስት አንባገነናዊ ጫና ምክንያት ለስደት እንደተዳረጉም ድምፃቸውን አሰምተዋል፡፡

ምንጭ፡- ሮይተርስ

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy