Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

በአውሮፓ ህብረት የኢትዮጵያ ተልዕኮ ቢሮ በብራሰልስ ተመረቀ

0 543

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

በአውሮፓ ህብረት የኢትዮጵያ ተልዕኮ ቢሮ በብራሰልስ ተመረቀ

በቤልጂየም ብራሰልስ የተገነባው በአውሮፓ ህብረት የኢትዮጵያ ተልዕኮ ቢሮ በጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ተመርቋል።

በምርቃት ስነ ስርአቱ ላይ በአውሮፓ ህብረት፣ በቤኔሉክስና ባልቲክ ሀገራት ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ተሾመ ቶጋን ጨምሮ ሌሎች ባለስልጣናት ተገኝተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ትናንት ማምሻውን በተጠናቀቀው የአውሮፓ ልማት ስብሰባ ላይ ለመካፈል ነበር ሰኔ 7 2008 ወደ ቤልጂየም ያቀኑት።

በብራሰልስ ቆይታቸውም ከተለያዩ የአውሮፓ ህብረት ባለስልጣናት ጋር መክረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያና የአውሮፓ ህብረት በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን ስትራቴጂያዊ ሰነድ ከህብረቱ ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ጃን ክላውድ ጀንከር ጋር መፈራረማቸውም የሚታወስ ነው።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy