Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ኢትዮጵያ ባላት ስትራቴጂያዊ አጋርነት ተፈላጊነቷ እያደገ መምጣቱን ጠ/ሚ ኃይለማሪያ ደሳለኝ ገለፁ

0 480

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ኢትዮጵያ ባላት ስትራቴጂያዊ አጋርነት ተፈላጊነቷ እያደገ መምጣቱን ጠ/ሚ ኃይለማሪያ ደሳለኝ ገለፁ

ሰኔ 09፣2008

ኢትዮጵያ  ባላት ስትራቴጂያዊ  አጋርነት ተፈላጊነቷ እያደገ  መምጣቱን ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማሪያ ደሳለኝ ገለፁ።

ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ  ከአውሮፓ  የልማት  ጉባኤ  ጎን ለጎን  በብራስልስ   የተለያዩ ሀገራትና ድርጅት መሪዎችን አነጋግረዋል። ውይይቱም የኢትዮጵን በአለም አቀፍ መድርክ ተቀባይነቷ  እያደገ  መምጣቱን ያሳየ መሆኑን ጠቅላይ ሚንስትሩ  ገልፀዋል።

ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማሪያም ከአውሮፓ  ህብረት ኮሚሽን ፕሬዝዳንት  ጃንክ ላውዴ ጃንከር ፣ከምክትል ፕሬዘዳንቷ  ፍሬዴሪካ ሞጋሪን ፣ከህብረቱ  ምክር ቤት   ፕሬዝዳንት  ዶናልድ ታሰን ፣ከአውሮፓ ህብረት የስደተኞች ጉዳይ ኮሚሽነር ዲሚትሪ ቫምፓሊስ ጋር  እንዲሁም  ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት  ዋና ፀሀፊ  ባንኪሙን ጋር  ተወያተዋል።

ጠቅላይ ሚንስትሩ እንዳሉት ውይይቱ የሀገሪቱን ስትራቴጃዊ  አጋርነት ያረጋገጠ  እንደነበር ገልፀዋል።

ኢትዮጵያ አሁን ላይ  ለብድርና  ልማት  ብቻ  ሳይሆን  ለንግድና ኢንቨስትመንት ተመራጭ ሀገር እየሆነች መምጣቷን ተናግረዋል።

ሀገሪቱ  ከተለያዩ አለም አቀፍ ድርጅቶችና ሀገራት ጋር የሚኖራት  ግንኙነት ከእርዳታ  ይልቅ ቴክኖሎጂ፣  ክህሎትና የእውቀት ሽግግር ቅድሚያ እንደምትሰጥ አስረድተዋል።

በዚህ  መስመር ከበርካቶች ጋር ከተራ ወዳጅነት  ያለፈ ስትራቴጃዊ  አጋርነት  የመስረተችው ኢትዮጵያ ከአውሮፓ፣ አሜሪካና  ቻይና ጋር  በእንዲህ አይነቱ  ስትራቴጂያዊ አጋርነት ከሚጠቀሱት ግንባር ቀደሞቹ  ናቸው።

ሪፖርተር፥ ብሩክ ያሬድ (ከቤልጄም ብራሰልስ)

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy