Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ኤጀንሲው በሀገር ላይ ጉዳት ሊያደርሱ የሚችሉ ከ165 በላይ የሳይበር ጥቃቶች ማክሸፉን አስታወቀ

0 545

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ኤጀንሲው በሀገር ላይ ጉዳት ሊያደርሱ የሚችሉ ከ165 በላይ የሳይበር ጥቃቶች ማክሸፉን አስታወቀ

ኤጀንሲው በሀገር ላይ ጉዳት ሊያደርሱ የሚችሉ ከ165 በላይ የሳይበር ጥቃቶች ማክሸፉን አስታወቀ

በሀገር ላይ ጉዳት ሊያደርሱ የሚችሉ ከ165 በላይ ዋና ዋና የሳይበር ጥቃቶች ማክሸፉን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ገለጸ።

ኤጀንሲው የ9 ወር የስራ አፈፃፀሙን ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ አቅርቧል።

ዋና ዳይሬክተሩ ሜጀር ጀኔራል ተክለብርሀን ወልደአረጋይ፥ ኤጀንሲው ሀገራዊ የሳይበር ኢንዱስትሪ ለማስፋፋት እየሰራ ይገኛል ብለዋል።

ዋና ዳይሬክተሩ የሳይበር ጥቃት የከፋ ጉዳት ሳያስከትል በመቆጣጣር እንዲሁም በቴሌ ኮሙዩኒኬሽን ተደራሽነት ላይ ጉዳት በማድረስ የማጭበበር የወንጀል ድርጊቶችንም ለመከላከል እና ሀገራዊ የሳይበር አቅምን በማሳደግ ረገድ ኤጀንሲው ባለፉት ዘጠኝ ወራት ያከናወናቸውን ስራዎች ሪፖርት አቅርበዋል።

የሚፈጸሙ የሳይበር ጥቃቶችን በመለየት የሚከላከል እና ምላሽ የሚሰጥ ኢትዮ ሰርጥ ማእከል በማቋቋም ወደ ስራ መግባቱን ያነሱት ዋና ዳይሬክተሩ፥ ባለፉት ዘጠኝ ወራትም በየደቂቃዎች በርካታ የሳይበር ጥቃቶች ቢኖሩም በሀገር ላይ ከፍተኛ ጉዳት ሊያደርሱ የሚችሉ ዋና ዋና ከ165 በላይ የተለያዩ የሳይበር ጥቃቶችን የመጠበቅ፣ ምላሽ የመስጠት እና የማክሸፍ ስራ መሰራቱን ገልጸዋል።

ከምክር ቤቱ ጥቃቶቹ እንዴት 165 ብቻ ሊሆኑ ቻሉ የሚል ጥያቄ የቀረበ ሲሆን፥ በየሰከንዱ በሚሊየን የሚደርስ የሳይበር ጥቃት ሊፈጸሙ ይችላሉ፤ ቁጥራቸው የተጠቀሰው ጥቃቶች በዋናነት በሀገር እና በዜጎች ላይ ጉዳት ሊያደርሱ የሚችሉ ጥቃቶች መሆናቸውን አንስተዋል።

እነዚህን ጥቃቶች አድኖ በመያዝ እንዲከሽፉ የማድረግ ዋና ዋና ተግባራት መከናወናቸውን ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።

ኤጀንሲው በቴሌ ኮሙዩኒኬሽን ዘርፍ ተደራሽነትን በማወክም ሲከናወኑ የነበሩ ማጭበርበር ተግባራት ሲከላከል መቆየቱንም ዋና ዳይሬክተሩ ሜጀር ጀኔራል ተክለብርሀን ወልደአረጋይ ተናግረዋል።

ለዚህም በተለይ የኢትዮ ቴሌኮም አገልግሎት ተደራሽነት ላይ ተጽእኖ በመፍጠር ከዘርፉ ከሚገኘው ከፍተኛ ገቢ ላይ ጉዳት ሲያደርሱ የነበሩትን የመከላከል ስራ ተሰርቷልም ብለዋል።

ከነዚህም ውስጥ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመሆን የመፍትሄ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ እና የቴሌኮም የማጭበርበር አዋጅ የማስፈጸሚያ ደንብ በማውጣት የተለያዩ ስራዎች መከናወናቸውንም በሪፖርታቸው አብራርተዋል።

በተለያዩ ጊዜያትም የዘመቻ ስራ በማካሄድ በጅግጅጋ፣ አዲስ አበባ፣ ሀረር እና ድሬደዋ ከተሞች እስክ 720 ሲም ካርዶችን መጠቀም በሚያስችሉ መሳሪያዎች በመታገዝ ከ404 በላይ የቴሌኮም ማጭበርበር ስራ ሲሰሩ የነበሩ 46 ተጠርጣሪዎች ለህግ መቅረባቸውንም ገልጸዋል።

በዚህ ማጭበርበር ተግባርም በመንግስት ላይ ከ1 ቢሊየን ብር በላይ ጉዳት መድረሱን ተረጋግጧል ነው ያሉት።

በተጨማሪም የብሄራዊ የካዳስተር ስርዓት ለመዘርጋት በአራት ክልሎች በሚገኙ ስድስት ከተሞች ከመሬት እና ከመሬት ይዞታ ጋር ተያይዞ ያሉ ስራዎችን በማጥናት እንዲመዘገቡ መደረጉንም አንስተዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ የካዳስተር ስርዓትም አገልግሎት ላይ እንዲውል ድጋፍ እየተደረገ ይገኛል ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ፥ በእነዚህ ተግባራትም ልምድ በመቅሰም በቀጣይ በሚከናወኑ ተግባራት ላይ ከፍተኛ አቅም እንደሚገኝ ገልጸዋል።

በአጠቃላይ በሳይበር ጥቃት ላይ በሚከናወኑ የመከላከል ተግባራት ውስጥ ሀገራዊ የሳበር ኢንዱስትሪ መገንባት እንደሚያስፈልግ ዋና ዳይሬክተሩ ሜጀር ጀኔራል ተክለብርሀን ወልደአረጋይ አስታውቀዋል።

በበላይ ተስፋዬ

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy