Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

እንግሊዝ ከአውሮፓ ህብረት እራሷን አገለለች

0 522

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

እንግሊዝ ከአውሮፓ ህብረት እራሷን አገለለች
ሰኔ 17፣2008
እንግሊዝ ባካሄደችው ታሪካዊ ህዝበ ውሳኔ እራሷን ከአውሮፓ ህብረት ለማግለል በጠባብ የድምፅ ልዩነት ወስናለች፡፡
ከአውሮፓ ህብረት እራሳችንን እናግልል ያሉት እንግሊዛውያን 52 በመቶ ሲሆኑ ቀሪዎቹ 48 በመቶ እንግሊዛውያን ግን የህብረቱ አባል ሆነን እንቀጥል በማለት ድምፃቸውን ሰጥተው ነበር፡፡
ኢንግላንድና ዌልስ ከህብረቱ መውጣትን የደገፉ ሲሆን ስኮላንድና ሰሜን አየርላንድ ደግሞ የህብረቱ አባል ሆኖ ለመቆየት ድምፃቸውን ሰጥተው ነበር፡፡
ከህብረቱ በመውጣታቸው ደስተኛ የሆኑት የUKIP ሀላፊ ናይጅል ፌራጅ እለቱን “የነፃነት ቀን” ብለው አሞካሽተውታል፡፡
በኢኮኖሚ ግዙፍነቷ ከአውሮፓ አገራት በሁለተኛ ደረጃ ላይ የምትገኘው እንግሊዝ የአውሮፓ ህብረት አባል ሆና እንድትቀጥል ወጥነው የነበሩት እንግሊዛውያን መገንጠሉ አይቀሬ ዱብ እዳ ሆኖባቸዋል፡፡
በህዝብ ውሳኔው 72 በመቶ ወይም ከ30 ሚሊዮን በላይ እንግሊዛውያን የተሳተፉነት ሲሆን በ24 ዓመታት የአገሪቱ የምርጫ ታሪክ ውስጥ የዜጎቹ ተሳትፎ ብዛት የመጀመሪያው ሆኗል፡፡
የእንግሊዝ መገልገያ ገንዘብ ፓውንድ ከዶላር አንፃር እንደ አውሮፓ አቆጣጠር ከ1985 ጀምሮ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ አሽቆልቁሏል፡፡
ምንጭ፡- ቢቢሲ

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy