Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ከታንዛንያ 74 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ወደ አገራቸው ተመለሱ

0 527

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ከታንዛንያ 74 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ወደ አገራቸው ተመለሱ

ሰኔ 08፣2008

በታንዛንያ በስደት ላይ የነበሩ 74 ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው ተመለሱ።

የዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት ባደረገው ድጋፍ ወደ አገራቸው የገቡት እነዚህ ስደተኞች በሕገ-ወጥ መንገድ ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመግባት ሲሞክሩ በታንዛንያ ፖሊስ ተይዘው በእሥር ቤት ለወራት የቆዩ ናቸው።

ከተመለሱት 74 ስደተኞች ውስጥ 53ቱ እድሜያቸው ከ18 ዓመት በላይ ሲሆኑ፣ ቀሪዎቹ ከ18 ዓመት በታች ናቸው ።

የኢትዮጵያና ታንዛንያ መንግሥታትን ጨምሮ በዓለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት አጋዥነት ወደ አገራቸው መመለሳቸውን የገለጹት ስደተኞቹ በህገ ወጥ አዘዋዋሪዎች ምክንያት የደረሱበት የማይታወቅ፣የሞቱና ሌሎች ለእንግልት የተዳረጉ ስደተኞች መኖራቸውን ገልጸዋል።

በያዝነው ዓመት በዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት ትብብር 1 ሺህ 657 ስደተኞች ከ10 አገሮች ወደ አገራቸው መመለሳቸውን በኢትዮጵያ የዓለም አቀፍ ስደተኞች ድርጅት ጽሕፈት ቤት ማስታወቁን የኢዜአ ዘገባ ያመለክታል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy