Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች የሚሰጡ መግለጫዎች ወቅታዊ ሊሆኑ ይገባል :-ም/ቤቱ

0 766

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች የሚሰጡ መግለጫዎች ወቅታዊ ሊሆኑ ይገባል :-ም/ቤቱ

ሰኔ 08፣2008

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ፅሕፈት ቤት በፅሕፈት ቤቱ የሚሰጡ መግለጫዎች ወቅታቸውን የጠበቁ መሆን እንደሚገባቸው በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የባህል ቱሪዝምና መገናኛ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አሳሰበ፡፡

በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የባህል፣ ቱሪዝምና መገናኛ ብዙሀን ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ  የመንግስት ኮሚንኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት የዘጠኝ ወር እቅድ አፈጻጸምን ገምግሟል።

ለቋሚ ኮሚቴው ሪፖርቱን ያቀረቡት የጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ ሚንስትር አቶ ጌታቸው ረዳ  ጽሕፈት ቤቱ በአገሪቱ በሚከሰቱ ሁነቶች የጋራ አጀንዳ ከመቅረጽ አንፃርና በየጊዜው በሚከናወኑ ጉዳዮች ዙሪያ በሚሰጡ መግለጫዎች ተመስርቶ በህዝብ ዘንድ የጋራ አመለካከት መፍጠር የሚያስችሉ ስራዎች ማከናወኑን ገልጸዋል።

የቋሚ ኮሚቴው እባላትም በቀረበው ሪፖርት መሰረት ጥያቄዎችን ያቀረቡ ሲሆን በጽሕፈት ቤቱ የስራ ኃላፊዎች ምላሽ ተሰጥዋል።

ቋሚ ኮሚቴው በሰጠው ግብረ መልስ ጽሕፈት ቤቱ የኮሚኒኬሽንና የሚዲያ ስራዎችን በተደራጀ የለውጥ ሰራዊት ለመምራት ያከናወናቸው ስራዎች፣ በጽሕፈት ቤቱ ማሻሻያ ሰነዶች፣ ወቅታዊ ጉዳዮች፣ በመንግስት ኃላፊዎች በተሰጡ መግለጫዎችና የህዝብ አስተያየት እንዲሁም ሌሎች ጉዳዮችን የዳሰሰ ጥናት በማድረግ ከጥናቱ በተገኙ ውጤቶችና በመፍትሔ ሀሳቦች ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት መምከሩን  በጠንካራ አፈጻጸም ገምግሟል።

ጽሕፈት ቤቱ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊዎች ከመመደብና ከማዘዋወር ረገድ ተቋማት የሚመደብላቸው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አለመቀበልና ተቋማት ድጋፍ አግኝተው የመረጃ ምንጭነት ሚናቸው በአግባቡ አለመወጣታቸው በጉድለት የሚታይ መሆኑን ገልጿል።

በጽሕፈት ቤቱ የሚሰጡ መግለጫዎች ወቅታቸውን ጠብቀው መውጣት እንደሚገባቸው ቋሚ ኮሚቴው አሳስቧል።

ሪፖርተር፥  ተስፉ ወልደገብርኤል

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy