Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

የማህፀን ውስጥ ዕጢ

0 4,548

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የማህፀን ውስጥ ዕጢ
(በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም ቱፈር)

የማህፀን ዕጢ የምንለው የካንሰርነት ባሕርይ የሌለው የማሕፀን ውስጥ ዐዥባጭ ሲሆን በአብዛኛው የሚከሰተው በወጣትነት ዕድሜ ላይ ነው፡፡ የማህፀን ውስጥ ዕጢ ወደ ማኅፀን ካንሰርነት የመለወጥ ዕድሉ እጅግ በጣም አናሳ ነው፡፡

የማሕፀን ዕጢ ከማሕፀን ግድግዳ ጡንቻዎች የሚነሳ ሲሆን የሴሎች ጤናማ ባልሆነ ሆኑታ ሲከፈሉ የሚመጣ ሆኔታ ነው፡፡ ይህ የማሕፀን ዕጢ በፍጥነት የሚያድግ ወይንም በዝግታ የሚያድግ ሊሆን ይችላል፡፡ አንዳንድ ጊዜም ተመልሶ በራሱ ሊጠፈም ይችላል፡፡
የማሕፀን ዕጢ በሴቶች ላይ እጅግ የተለመደ በመሆኑ ምክንያት ከ4 ሴቶች ሦስቱ በሕይወት ዘመናቸው የማሕፀን ዕጢ እንደሚኖራቸው ጥናቶች ያሳያሉ፡፡ ነገር ግን ምልክት ስለማያሳዩ እንዳላቸውም የማወቅ ዕድል የላቸውም፡፡ በአብዛኛው የሚገኘው በድንገት በሚደረግ ምርመራ ነው፡፡

የማሕፀን ዕጢ ምልክቶች

የማኅፀን ዕጢ በአብዛኛው ምንም ዓይነት ምልክት የማያሳይ ቢሆንም በአንዳንድ ሰዎች ላይ የሚከሰቱ ምልክቶች እንዚህ ናቸው፡፡
• ከፍተኛ የሆነ የወር አበባ መብዛት
• ከሰባት ቀናት በላይ የሚቆይ የወር አበባ ማየት
• ማሕፀን አካባቢ ግፊት መሰማት ወይንም ሕመም
• ቶሎ ቶሎ የውሃ ሽንት መምጣት
• የሆድ ድርቀት
• የጀርባ እና የዕግር ሕመም ስሜት
• አልፎ አልፎ ከፍተኛ የሆነ ሕመም (አጣዳፊ) የሚያስከትል ሲሆን ይህም የሚሆነው የደም ዝውውር በሚቀንስ ጊዜ/በሚቋረጥ ጊዜ ነው፡፡

የማሕፀን ዕጢ ለምን ይከሰታል

ይህ ነው የሚባል ዕርግጥ ምክንያት የሌለው ቢሆንም ጥናቶች የሚያመለክቷቸው ከሆርሞኖች እና የጀኔቲክ ሁኑታዎች ጋር ተያያዥነት እንዳላቸው ነው፡፤

ለማሕፀን ዕጢ ተጋላጭነት የሚጨምሩ ሁኔታዎች

• ከዘር፡- እናት ወይንም እሕት የማሕፀን ዕጢ ወደ ዘር ካላቸው ተጋላጭነትን ይጨምራል፡፡
• ጥቁር ዘር፡- ጥቁር ሴቶች በአብዛኘው ተጋላጭነታቸው ይጨምራል፡፡
• በልጅነት የወር አበባን ያዩ ከሆነ እና አመጋገብ ናቸው፡፡
የማኅፀን ዕጢ ለከፋ የጤና ችግር የሚዳርግ ባይሆንም የደም ማነስ እና ምቾት ማጣትን ግን ሊያስከትል ይችላል፡፡

የማሕፀን ዕጢ እና እርግዝና

የማሕፀን ዕጢ በአብዛኛው እርግዝናን የማይቃረን ቢሆንም አንዳንዴ ዕጢው በሚገኝበት ቦታምክንያት በጥቂት ሰዎች ላይ እርግዝናን እንዳይፈጠር መንስዔ ይሆናል፡፡ ይህ በመሆን ጊዜ ሐኪምን በማማከር ከእርግዝና በፊት መደረግ ያለባቸውን ቅድመ ሆኔታዎች ማድረግ ተገቢ ነው፡፡

ሐኪምዎን ማማከር የሚገባዎ መቼ ነው?

• የማያቋርጥ የማሕፀን አካባቢ ሕመም ካለ
• ከፍተኛ ሕመም ያላቸውና በብዛት የሚያስቸግሩ የወር አበባ ጊዜያት
• ከወር አበባ ፅዳት ውጪ የደም መፍሰስ
• በግብረ ስጋ ግኝኑነት ጊዜ የሕመም ስሜት ከተሰማዎተግ
• የሆድ ዕብጠት ካለዎዘ
• የውኃ ሽንትን ማስወገድ መቸገር

እጅግ ከፍተኛ የሆነ ድንገተኛ የማኅፀን አካባቢ ሕመም ካለዎትና ከፍተኛ የደም መፍሰስ የሚኖር ከሆነ በአፋጣኝ ወደ ሐኪም እንዲሄዱ ይመከራል፡

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy