Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

የሰበታ – መኤሶ – ደወሌ የባቡር መስመር በመስከረም ወር ወደ አገልግሎት ይገባል

0 465

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የሰበታ – መኤሶ – ደወሌ የባቡር መስመር በመስከረም ወር ወደ አገልግሎት ይገባል

የሰበታ – መኤሶ – ደወሌ የባቡር መስመር ፕሮጀክት በመጪው መስከረም ወር ሙሉ በሙሉ ወደ አገልግሎት እንደሚገባ ተነገረ።

የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶክተር ኢንጂነር ጌታቸው በትሩ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንዳሉት፥ ፕሮጀክቱ በአሁኑ ወቅት ከ95 በመቶ በላይ ተጠናቋል።

ፕሮጀክቱ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችለውን የኤሌክትሪክ አቅርቦት ለማግኘትም ዝግጅቶች እየተጠናቀቁ መሆኑንም ነው ዋና ስራ አስፈጻሚው የገለጹት።

እነዚህ ስራዎች በአጭር ጊዜ ውስጥ የሚጠናቀቁ በመሆናቸው የባቡር መስመሩ በ2009 ዓመተ መህረት መጀመሪያ ወደ አገልግሎት ይገባል ብለዋል።

ፕሮጀክቱ ሙሉ በሙሉ ስራ ሲጀምርም የሀገሪቱን የወጪ ገቢ ንግድ ከማቀላጠፍ ባሻገር፥ የቱሪዝም ዘርፉን እድገት ለማጠናከር የጎላ ሚና እንደሚኖረው ተናግረዋል።

 

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy