Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት 245 የአልሻባብ ታጣቂዎችን ደመሰሰ

0 5,385

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ሰኔ 2፣2008

የኢፌዲሪ መከላከያ እና የሶማሊያ ሰራዊት የአልሻባብን የማጥቃት እርምጃ በማክሸፍ  245   የአልሻባብ ታጣቂዎችን ደመሰሱ።

ዛሬ ንጋት ላይ በሂራን ዞን ሀልገን ከተማ እና አካባቢውን በተቆጣጠረው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ላይ የማጥቃት ሙከራ ያደረገው አልሻባብ አብዛኛው ሀይሉ ተደምስሷል፡፡

ሰራዊቱ ቀሪውን እና የተበታተነውን የአልሻባብ ሀይልን የመደምሰስ ስራውን አጠናክሮ መቀጠሉ  ተገልጿል፡፡

ከተለያዩ ቦታዎች ሀይሉን አሰባስቦ የመጣው እና በአጥፍቶ ጠፊ ተሽከርካሪዎች እና ፈንጂዎች የታገዘው አልሻባብ በአራት አቅጣጫ ማጥቃት ቢጀምርም የኢትዮጵያ መከላከያና የሶማሊያ ስራዊት በወሰዱት የመከላከል እና ፀረ ማጥቃት እርምጃ ተደምስሷል፡፡

በተወሰደው ጠንካራ የማጥቃት እርምጃ አምስት ከፍተኛ የአልሸባብ አመራሮችን ጨምሮ 245 ታጣቂዎቹ ተደምስሰውበታል ብሏል መከላከያ ሚኒስቴር በላከው መግለጫ፡፡

በጥቃቱ በቡድኑ ላይ ከደረሰው ሰብአዊ ኪሳራ በተጨማሪ በርካታ ቁጥር ያላቸው የነፍስ ወከፍና የቡዱን መሳሪያዎች እንዲሁም ብዛት ያላቸው ተተኳሾች ተማርከዋል።

የተማረኩት መሳሪያዎች የመደበኛ ሰራዊት ትጥቆች ሲሆኑ መጠናቸው እንዴት እና ከማን እንደተገኙ ዝርዝር መረጃውን በቀጣይ እንደሚገልጽ የኢፌዲሪ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy