Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

የኤርትራ መንግስት በዜጎቹ ላይ እየፈጸመ ያለውን ግፍ እንዲያቆም የኤርትራ ስደተኞች ጠየቁ

0 673

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የኤርትራ መንግስት በዜጎቹ ላይ እየፈጸመ ያለውን ግፍ እንዲያቆም የኤርትራ ስደተኞች ጠየቁ

ሰኔ 16፣2008

የኤርትራ መንግስት በዜጎቹ ላይ እየፈጸመ ያለው ግፍና በደል እንዲያቆም የዓለም ማህበረሰብ ግፊት እንዲያደርግ በኢትዮጵያ የሚገኙ የኤርትራ ስደተኞች ጠየቁ፡፡

የመንግስታቱ ድርጅት የሰብዓዊ መብት አጣሪ ኮሚሽን በኤርትራ መንግስት የሰብዓዊ መብት ጥሰትን አስመልክቶ ያወጣውን ሪፖርት በመደገፍም ስደተኞቹ አዲስ አበባ በሚገኘው የአፍሪካ ህብረት ዋና ጽ/ቤት ፊት ለፊት ሰላማዊ ሰልፍ አድርገዋል፡፡

ኢሳያስ አፈወርቄ ለአለም አቀፍ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ሊቀርቡ እንደሚገባም የኤርትራ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ ሊቀመንበር አቶ በሽር አይዛክ አብደላ ጠይቀዋል።

ሰልፈኞቹ ያሰባሰቡትን የድጋፍ ፊሪማ ለአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ተወካይ አስረክበዋል።

በበተያያዘ ዜና በትግራይ አራት የስደተኞች ማዕከላት የሚገኙ ከ50ሺ በላይ የኤርትራ ስደተኞችም ዛሬ ከማለዳው 12 ሰዓት ጀምሮ የሻቢያን የግፍ አገዛዝን በመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ አካሄደዋል፡፡

የኤርትራ መንግስት  በዜጎቹ ላይ እያደረሰ ያለውን የሰብአዊ መብት ጥሰት አስመልክቶ የተባባሩት መንግስት ድርጅት የሰብአዊ መብት ኮሚሽን በቅርቡ ያወጣው ሪፖርት ተገቢ መሆኑን ሰልፈኞቹ ባሰሙት መፈክርና በሰጡት አስተያየት ገልጸዋል፡፡

በሚደርስባቸው ግፍ ምክንያት አገራቸውን ለመልቀቅ መገደዳቸውን ያስታወቁት ሰልፈኞቹ መሰደድ ያልቻሉ ኤርትራዊያን ወንድሞቻቸው በአስገዳጅ የውትድርና ዘመቻ ህይወታቸውን ለመግፋት ተገደው እንዳሉ ጠቁመዋል፡፡

የኤርትራ  መንግስት በዜጎቹ ላይ እየፈጸመ ያለው ግፍና ግድያ እንዲያቆም የዓለም ማህበረሰብ ግፊት እንዲያደርግበት ስደተኞቹ ጠይቀዋል፡፡

ሰላማዊ ሰልፉን ያካሄዱት በማይዓይኒ፣ ዓዲ ሓሩሻ፣ ሕጻጽና ሹመልባ በተባሉት አራት የስደተኞች ማዕከላት የሚገኙ የኤርትራ ስደተኞች ናቸው።

ኢቢሲና ኢዜአ

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy