Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

የካናዳ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ ያሉ የኢንቨስትመንት አማራጮችን እያጠኑ ነው።

0 473

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የካናዳ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ ያሉ የኢንቨስትመንት አማራጮችን እያጠኑ ነው።

ሰኔ 09፣2008

የካናዳ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ በኢንቨስትመንት ለመሰማራት የሚያስችሉ  አማራጮችን እያጠኑ ነው።

የኢትዮ-ካናዳ የንግድ ውይይት በአዲስ አበባ እየተካሔደ ይገኛል።

13 አባላትን የያዘው የካናዳ የባለሐብቶች ቡድን በኢትዮጵያ ያለውን የኢንቨስትመንት አማራጮችን ለመመልከት ነው የመጡት፡፡

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ባለሀብቶቹ በኢትዮጵያ ቢሰሩ ውጤታማ ሊሆኑ በሚችሉባቸው መስኮች ዙሪያ ገለፃ አድርጎላቸውል፡፡

የኮሚሽኑ ምክትል ዳይሬክተር አቶ አበበ አበባየሁ የካናዳ ባለሐብቶች በተለይ በጨርቃ ጨርቅ፣በቆዳ፣በታዳሽ ኃይልና በመሰረተ ልማት መስኮች ቢሰማሩ ውጤታማ እንደሚሆኑ ለባለሐብቶቹ ነግረዋቸዋል፡፡

የንግድ ለንግድ ስብሰባው ከሰዓት በኋላ ቀጥሎ የካናዳና የኢትዮጵያ ባለሐብቶች በሽርክና መስራት በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

 

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy