# መልካም_እድል_ለኢትዮጵያ !!! # የበለጸገች_ኢትዮጵያ #
ኢትዮጵያ አፍሪካን ወክላ እጩ የሆነችበት የመንግስታቱ ተለዋጭ የፀጥታ ም/ ቤት ምርጫ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጽ/ ቤት መቀመጫ በሆነችው # ኒውዮርክ ከተማ በነገው እለት ይካሔዳል። የተባበሩት፡መንግስታት የፀጥታው፡ምክር ቤት፡ 5 ቋሚ አባል አገራት (ኣሜሪካ፣እንግሊዝ፣ቻይና፣ሩሰያ እና ፈረንሳይ) ሲኖሩት ለሁለት አመታት በአባልነት የሚያገለግሉ እና ከሁሉም አህጉራት የተውጣጡ 10 አገራት # ተለዋጭ የፀጥታው ምክር ቤት አባላት በመባል የሚታወቁትም በአባልነት ይካተታሉ ። #ኢትዮጵያ አፍሪካን በመወከል ተለዋጭ የፀጥታው ምክር ቤት አባል እንድትሆን የአፍሪካ ህብረት አባል ሀገራት በሙሉ ድምፅ የወከሏት ሲሆን # በውጭ _ጉዳይ _ሚንስትር _ ዶክተር _ቴድሮስ _ኣድሓኖም አማካኝነት በመላው አለም የምረጡኝ ቅስቀሳም ስታካሂድ ቆይታለች ምርጫው በነገው እለት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጽ/ ቤት መቀመጫ በሆነችው # ኒውዮርክ ከተማ ይካሄዳል።በምርጫውም #ኢትዮጵያ የፀጥታውም ምክር ቤት ተለዋጭ አባል ሆና እንደምትመረጥ ይጠበቃል። #መልካም_እድል_ለኢትዮጵያ