ሲሲቲቭ የተሰኘው የቴሌቭዥን ጣቢያ ዛሬ እንደዘገበው የአውሮፓ ሕብረት በ12 የአፍሪካ ሃገራት አየር መንገዶች ላይ በሕብረቱ የአየር ክልሎች እንዳይበሩ እገዳ አስተላለፈ::
ሕብረቱ ኤርትራን ጨምሮ በ12 ሃገራት ላይ እገዳውን ሲጥል ሃገራቱም
1ኛ . ቤኒን 2ኛ. ኮንጎ ሪፐብሊክ 3ኛ. ዴሞክራሲያ ሪፐብሊክ ኮንጎ 4ኛ. ጅቡቲ 5ኛ. ኢኳቶሪያል ጊኒ 6ኛ. ጋቦን 7ኛ. ላይቤሪያ 8ኛ. ሊቢያ 9ኛ. ሞዛምቢክ 10ኛ. ሴራሊዮን 11ኛ. ሱዳን ናቸው::
የአውሮፓ ሕብረት የ214 አየር መንገዶችን የደህንነት ደረጃ የመረመረ ሲሆን ከአፍሪካ 12 እንዲሁም ከሌሎች ዓለም ሃገራት 7 በጥቅሉ የ19 ሃገራትን አየር መንገዶች አግዷል::
ለረዥም ጊዜያት እገዳ ተጥሎበት የቆየው የዛምቢያና የማዳጋስካር አየር መንገዶች በአውሮፓ እንዲበሩ የተፈቀደ ሲሆን ከላይ የተጠቀሱት ሃገራት አየር መንገዶች ለመንገደኞች ደህንነት አስጊዎች ናቸው በሚል በክልሉ እንዳይበሩ መታገዱን ከሲሲቲቭ ያገኘችው መረጃ ያመለክታል:;