NEWS

በአውሮፓ ህብረት የኢትዮጵያ ተልዕኮ ቢሮ በብራሰልስ ተመረቀ

By Admin

June 17, 2016

በአውሮፓ ህብረት የኢትዮጵያ ተልዕኮ ቢሮ በብራሰልስ ተመረቀ

በቤልጂየም ብራሰልስ የተገነባው በአውሮፓ ህብረት የኢትዮጵያ ተልዕኮ ቢሮ በጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ተመርቋል።

በምርቃት ስነ ስርአቱ ላይ በአውሮፓ ህብረት፣ በቤኔሉክስና ባልቲክ ሀገራት ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ተሾመ ቶጋን ጨምሮ ሌሎች ባለስልጣናት ተገኝተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ትናንት ማምሻውን በተጠናቀቀው የአውሮፓ ልማት ስብሰባ ላይ ለመካፈል ነበር ሰኔ 7 2008 ወደ ቤልጂየም ያቀኑት።