Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

አስገዳጅ ደረጃ ውስጥ ያልገቡ የታሸጉ ውሃዎች ሁለት የፌደራል ተቋማትን እያወዛገቡ ነው

0 1,764

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

አስገዳጅ ደረጃ ውስጥ ያልገቡ የታሸጉ ውሃዎች ሁለት የፌደራል ተቋማትን እያወዛገቡ ነው

አስገዳጅ ደረጃ ውስጥ ያልገቡ የታሸጉ ውሃዎች ሁለት የፌደራል ተቋማትን እያወዛገቡ ነው

አስገዳጅ ደረጃ ውስጥ ያልገቡ የታሸጉ ውሃዎች የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኤጀንሲንና የኢትዮጵያ ምግብ፣ መድሃኒትና ጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣንን እያወዛገቡ ነው።

የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኤጀንሲ፥ በቁጥጥር ችግር ምክንያት የአስገዳጅ ደረጃን ሳያገኙ ገበያ ላይ የሚውሉ የታሸጉ ውሃዎች እየተበራከቱ መምጣቱን በዳሰሳዬ አረጋግጫለው ይላል።

የኢትዮጵያ ምግብ፣ መድሃኒትና ጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣን በበኩሉ ቁጥጥሩን በማድረግ ወደ መስመር እንዲገቡ እያደረኩ ነው፤ ኤጀንሲው ተገቢውን ግንዛቤ እየሰጠ ባለመሆኑ ነው ችግሩን መፍታት አዳገች የሆነው ብሏል።

በአሁኑ ወቅት አብዛኛው የምግብና መድሀኒት ነክ ምርቶች አስገዳጅ ደረጃ ውስጥ እንዲገቡ እየተደረጉ ነው።

ይህም በኢትዮጵያ ደረጃዎች ኤጀንሲ ምዘና ተደርጎ የሚፈለገውን ንጥረ ነገር ወይም ሌላ በውስጡ ያሉ ውህዶችን ይዘትና መጠን የሚለይበት ነው።

ምዘና ተደርጎ ጥራቱ ሲረጋገጥ የደረጃዎች ኤጀንሲ ምልክትን አግኝቶ ገበያ ላይ እንዲወጣ የሚያዝ ነው።

በዚህ እረገድ አስገዳጅ ደረጃዎች ውስጥ ከገቡት ውሃ አንዱ ነው።

የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኤጀንሲ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ይስማ ጅሩ፥ አሁን ላይ 48 የውሃ አምራች ተቋማት በምዘናዎች የተፈተሹ ናቸው።

ይሁን እንጂ በቅርቡ በተደረገ ዳሰሳ ጠቅላላ የውሃ አምራች ተቋማት ከ80 በላይ ደርሰዋል ያሉት አቶ ይስማ፥ ከእነዚህ ውስጥ አስገዳጅ ደረጃን ሳያሟሉ ገበያ ውስጥ የገቡ እና ጥራታቸው ያልተጠበቀ የውሃ ምርቶች ገበያ ውስጥ እንዳሉ ተናግረዋል።

አቶ ይስማ፥ ለዚህ ችግር በርካታ ምክንያቶች ቢኖርም አስፈላጊው ቁጥጥር በተገቢው ደረጃ አለመደረግ የሚለውን በዋናነት አንስተዋል።

ዳሰሳ አድርገው ይህን ለሚቆጣጠረው የኢትዮጵያ ምግብ፣ መድሃኒትና ጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣን መላካቸውንም ያነሱት ሃላፊው፥ የቁጥጥሩ ስራ የባለስልጣኑ እንደሆነ እና ውጤቱ ግን በሚፈለገው ደረጃ እንዳልሆነ ነው የነገሩን ።

የኢትዮጵያ ምግብ፣ መድሃኒትና ጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣን በበኩሉ፥ በአስገዳጅ ደረጃዎች የሚያልፉ የታሸጉ ውሃዎች ቁጥር እየጨመረ መጥቷል ብሏል።

በባለስልጣኑ የምግብ፣ ጤና እና ጤና ነክ ተቋማት ኢንስፔክሽን ዳይሬክተር አቶ አብነት ወንድሙ፥ ከዚህ ውጭ ስለተባለው የታሸጉ ውሃዎች የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኤጀንሲ የዳሰሳ ጥናት ለባለስልጣኑ እንዳልደረሰው ተናግረዋል።

በእርግጥም ችግሩ በከፊል መኖሩን የሚያነሱት ዳይሬክተሩ፥ ይህም በኤጀንሲው ሊሰጥ የሚገባው የግንዛቤ ስራ በተገቢው ባለመሰራቱ የመጣነው ይላሉ።

በምዘና ስርዓቱ ውስጥ ማለፍ ጥቅሙ ለሁሉም ሆኖ ሳለ በዚህ ረገድ ተጨባጭ ግንዛቤ እየተፈጠረ አይደለም ሲሉም ዳይሬክተሩ ይናገራሉ።

በዚህ ሂደት ውስጥ ታዲያ የደረጃ ምልክቱን ያልተጠቀሙ የውሃ ተቋማት ገበያ ላይ ውለው የምናይ ሲሆን፥ ይህ ደግሞ ለህገ ወጦች መንገድ የሚከፍት ነው።

የኢትዮጵያ ምግብ፣ መድሃኒትና ጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣን፥ በቂ ግንዛቤ መስጠት እየተገባ ግንዛቤው መፍጠር ካልተቻለ ተቅማቱ ወደዚህ መስመር የሚመጡበት እድል ጠባብ ነው።

የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኤጀንሲ ግን በሁሉም መንገድ የግንዛቤ መፍጠረ ስራው በስፋት እየተሰራ መሆኑንና በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አንስቷል።

በባለስልጣኑም በኩል በቁጥጥር ሂደት ተገኝተው ወደ መስመር እንዲገቡ መደረጉንና ያልገቡት ደግሞ ምርት እንዲያቋርጡ ተደረጓል።

ይሁን እንጂ አሁንም ባለስልጣኑ ጥናት እያደረገና የተባሉትን ዳሰሳዎች ከግምት በማስገባት ተቋማቱ ወደ ምዝና እንዲገቡ እናደርጋለን ብሏል።

ሁለቱ ተቋማት አስገዳጅ ደረጃ ውስጥ ባልገቡ የታሸጉ ውሃዎች ምክንያት ልዩነት ቢኖራቸውም በቀጣይ ችግሩን ለመፍታት በጋራ መስራት መፍትሄ መሆኑን ተቀብለዋል።

ሁለቱም ተቋማት በቅርቡ በመገናኘት በችግሩ ላይ እንደሚነጋገሩ እና የውሃ ተቋማት በምዘናው የማያልፉ ከሆነ እርምጃ ወደ መውሰዱ እንገባለን ብለዋል።

እንደ ሃላፊዎቹ ከሆነ ከዚህ በኋላ ማንኛውም የታሸገ ውሃ የምዘና ማረጋገጫን ሳያገኝ ገበያ ላይ እንዳይውል ይደረጋል።

ህብረተሰቡም የታሸገ ውሃ ሲገዛ የደረጃዎች ማረጋገጫ ምልክት ተመልክቶ እንዲገዛም ሃላፊዎቹ አሳስበዋል።
በሀይለኢየሱስ ስዩም

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy