ኢትዮጵያ ዘላቂ የልማት ግቦችን እንደምታሳካ ጠ/ ሚ ኃይለማርያም ገለጹ
ሰኔ 09፣ 2008
ኢትዮጵያ በዘላቂ የልማት ግቦች ላይ የተቀመጡ አጀንዳዎችን የመፈፀም ብቃት እንዳላት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ገለፁ፡፡
የአውሮፓ የልማት ጉባኤ በቤልጀም ብራሰልስ እየተካሄደ ነው፡፡
በመድርኩ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ እንደተናገሩት ኢትዮጵያ የልማት ግቦችን ለማሳካት ከሀገሪቱ ዕቅዶች ጋር በማስተሳሰር እየሰራች ነው፡፡
እያስመዘገበችው ያለው የኢኮኖሚ እድገትም ግቦቹን ለማሳካት ያስችላታል ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡
ለዘላቂ ልማት ግቦች ስኬት ከመንግስት ጥረት ጎን ለጎን የዓለም አቀፉ ማህበረስብ አጋርነት እንደሚያስፈልግም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አብራርተዋል፡፡
የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ምክትል ፕሬዝዳንት ፌዴሪካ ሞጎሪኒ በበኩላቸው ህብረቱ ግቦችን የሚያሳካ ትብብር ለማድረግ ቁርጠኛ መሆኑን ተናግረዋል።
በዚህ ጉባኤ ላይ የተለያዩ አገራት መሪዎች ለዘላቂ የልማት ግቦች ስኬታማነት ያከናወኑትን ተግባራት የተመለከተ ማብራሪያ አቅርበዋል፡፡
ሪፖርተር፡- ብሩክ ያሬድ( ከቤልጄም ብራስልስ)