Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

እንኳን_ደስ _ አለን ኢትዮጵያ ከሰአታት በፊት ኒውዮርክ በሚገኘው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በተካሔደው 32 ኛው የመንግስታቱ የፀጥታ ምክር ቤት ጉባኤ ላይ በተደረገው የተለዋጭ አባላት ምርጫ ከ190 አገራት ድምፅ 185 ቱ በማግኘት በከፍተኛ ውጤት እ.አ.አ ከ 2017 ጀምሮ ለሁለት አመታት በአባልነት ተቀላቅላለች።

0 1,017

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

እንኳን_ደስ _ አለን ኢትዮጵያ ከሰአታት በፊት ኒውዮርክ በሚገኘው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በተካሔደው 32 ኛው የመንግስታቱ የፀጥታ ምክር ቤት ጉባኤ ላይ በተደረገው የተለዋጭ አባላት ምርጫ ከ190 አገራት ድምፅ 185 ቱ በማግኘት በከፍተኛ ውጤት እ.አ.አ ከ 2017 ጀምሮ ለሁለት አመታት በአባልነት ተቀላቅላለች።

*የተባበሩት መንግስታት የፀጥታ ምክር ቤት***

የተባበሩት፡መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት 5 ቋሚ አባል አገራት (ኣሜሪካ፣እንግሊዝ፣ቻይና፣ሩሰያን ፈረንሳይን) ሲኖሩት ለሁለት አመታት በአባልነት የሚያገለግሉ እና ከሁሉም አህጉራት የተውጣጡ 10 አገራት ተለዋጭ የፀጥታው ምክር ቤት አባላት በመባል የሚታወቁ ናቸው።

***ኢትዮጵያና የአፍሪካ ውክልና***

የአፍሪካ ህብረት ባሳለፍነው ጥር ወር ኢትዮጵያ አፍሪካን በመወከል የመንግስታቱ ድርጅት በሚደረገው የተለዋጭ ምክር ቤት ምርጫ ላይ እንድትሳተፍ በሙሉ ድምጽ ከወሰነበት ጊዜ አንስቶ በውጭ ጉዳይ ሚንስትር ዶ/ር ቴድሮስ አድሓኖም አማካኝነት ቅስቀሳ ስታካሒድ ቆይታለች።

**የፀጥታው ምክር ቤት ተለዋጭ አባልነት**

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የመተዳደሪያ ቻርተር እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1965 በተደረገ መሻሻያ የፀጥታው ምክር ቤት ተለዋጭ አባላት ቁጥር ከ6 ወደ 10 ከፍ ያደረገ ሲሆን እነዚህም 10 ሀገራት በየዓመቱ በሚደረግ ምርጫ አምስት አምስት ሀገራትን ለሁለት በመክፈል በሁለት ዙር በየሁለት ዓመቱ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ተለዋጭ አባል ለመሆን የሚወዳደሩና የተወዳደሩት ሀገራት ምርጫውን ለማሸነፍ የተባበሩት መንግስታት ጠቅላላ ጉባዔ አባላት ውስጥ ሁለት ሶስተኛ (2/3) ድምፅ ማግኘት ይጠበቅባቸዋል።

*** ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ጥበቃ ምክር ቤት ተለዋጭ አባልነቷ***

√ በአለም አቀፋዊ ትብብርና በጋራ ሰላምና ደህንነት ላይ ያላትን የጸና አቃም አጠናክራ ትቀጥላለች። √ የአፍሪካን ጥቅሞች ለማስጠበቅ የምታደርገውን እንቅስቃሴ አጠናክራ ትቀጥላለች።

*** የአዲስ ተመራጭ ሀገራት የስራ ዘመን**

√ዛሬ ለተለዋጭነት የተመረጡ ተለዋጭ አባል ሀገራት እ .አ .አ ታህሳስ 2017 ቦታቸውን ተረክበው ለቀጣይ ሁለት ዓመታት የሚያገለግሉ ሲሆን ኢትዮጵያም አንጎላ ለሁለት ዓመታት ያገለገለችበት ስፍራ ተረክባ በተለዋጭ አባልነት ትቀጥላለች።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy