Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

የቀድሞ የገላን ከተማ ከንቲባን ጨምሮ የስራ ሀላፊ የነበሩ 12 ግለሰቦች በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ዋሉ

0 537

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የቀድሞ የገላን ከተማ ከንቲባን ጨምሮ የስራ ሀላፊ የነበሩ 12 ግለሰቦች በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ዋሉ

የቀድሞ የገላን ከተማ ከንቲባን ጨምሮ የስራ ሀላፊ የነበሩ 12 ግለሰቦች በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ዋሉ

የቀድሞ የገላን ከተማ ከንቲባን ጨምሮ በተለያዩ ጽህፈት ቤት ሀላፊ የነበሩ 12 ግለሰቦች በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ዛሬ በቁጥጥር ስር ዋሉ።

የኦሮሚያ ክልል ስነ ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ታከለ አንኮሳ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት፥ የቀድሞ የከተማዋ ከንቲባ አቶ ሙሉጌታ ከበደ እና የከተማዋ የኢንቨስትመንት ጽህፈት ቤት ሀላፊ፣ የመሬት ልማት ማኔጅመንት ጽህፈት ቤት ሀላፊ፤ የከተማዋ ካቢኔና ሌሎችም በሀላፊነትና በባለሙያነት ሲሰሩ የነበሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለዋል።

ኮሚሽኑ በእነዚህ ግለሰቦች ላይ ከወራት በፊት ምርመራ ሲያደርግ እንደቆየና በስራ ሀላፊነታቸው ወቅት ከኢንቨስትመንት ፈቃድ አሰጣጥ ጋር ተያይዞ፣ በባቡር መንገድ ግንባታ ምክንያት ለተፈናቀሉ አርሶ አደሮች የሚገባውን የካሳ ክፍያ አለመክፈልና ለራስ መጠቀም፣ ተተኪ ቦታዎችን ለማይገባው ግለሰብ መስጠት፣ የቀድሞ ይዞታ ያልነበራቸውን ሰዎች እንደነበራቸው ማድረግና መሰል ወንጀሎችን ፈጽመዋል በሚል በሙስና መጠርጠራቸው ተጠቁሟል።

ከዚህ በተጨማሪ በከተማዋ በተለያዩ ጊዜ ይሰሩ የነበሩትን የከተማዋ ፕሮጀክቶች የመንግስትን መመሪያ ደንብና የፋይናንስ ህጉን ባልተከተለና ጥራቱን ባልጠበቀ መንገድ እንዲሰራ በማድረግ ከጥቅሙ መጋራት የሚለው ሌላኛ ካስጠረጠራቸው ወንጀል ውስጥ ይገኛል።

ኮሚሽኑ እነዚህን የምርመራ ውጤቶች መነሻ በማድረግ ነው ዛሬ በቁጥጥር ስር ያዋልኳቸው ብሏል።

በግለሰቦቹ ላይ የሚደረገው ምርመራ አሁንም የቀጠለ ሲሆን፥ ባለው መረጃ መሰረት በነገው እለት ፍርድ ቤት የሚቀርቡ ይሆናል።

ግለሰቦቹ የተጠረጠሩበት የሙስና ወንጀልን ጨምሮ በሌሎችም የሙስና ተግባራት ላይ ተሳትፈዋል ተብለው የሚጠረጠሩ ግለሰቦችንም ለሚያዝ ክትትል እየተደረገ ነው ተብሏል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy