“ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት ተለዋጭ አባል ሆና እንድትመረጥ የአፍሪካ ህብረት አባል አገራት ላደረጉት ድጋፍ እናመሰግናለን” ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ******************** ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በሞዛምቢክ ይፋዊ የስራ ጉብኝት በማድረግ ላይ ናቸው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከአገሪቱ ፕሬዝዳንት ፊሊፕ ኒዩስ ጋር በሁለቱ ሀገራት የጋራ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል። ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት ተለዋጭ አባል ሆና እንድትመረጥ ሞዛምቢክ እና የአፍሪካ ህብረት አባል አገራት ላደረጉት ድጋፍ በማመስገን ኢትዮጵያ በፀጥታው ምክር ቤት ውክልናዋ የአህጉሪቱን ጥቅሞች ለማስጠበቅ ጥረት እንደምታደርግ እና የአህጉሪቱ ችግር የሆኑትን የአየር ንብረት ለውጥ፣ ድህነትና ስራ አጥነት፣ የሰላምና መረጋጋት እጦት፣ ሽብርተኝነት፣ ህገወጥ ስደትና የመሳሰሉትን ችግሮች መዋጋትና ጉዳቱን መቀነስ ትኩረት የሚሰጠው ጉዳይ በመሆናቸው ችግሮቹን ለመፍታት ደግሞ ከመቼውም ጊዜ በላቀ ትብብርና ቁርጠኝነት መስራት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።
- Comments
- Facebook Comments
Follow Us @ethiopiaprosperous
porn videos