Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

በባህር ዳር አለማቀፍ ስታዲየም በዲያስፖራውና በአመራሩ መካከል የተካሄደ የእግር ኳስ ጨዋታ የዲያስፖራው ቡድን 5ለ2 በማሸነፍ ተጠናቀቀ፡፡

0 525

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

በባህር ዳር አለማቀፍ ስታዲየም በዲያስፖራውና በአመራሩ መካከል የተካሄደ የእግር ኳስ ጨዋታ የዲያስፖራው ቡድን 5ለ2 በማሸነፍ ተጠናቀቀ፡፡

በጨዋታው የተገኙት የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር የተከበሩ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው እንደገለፁት የስፖርት ዋና ዓላማው ወንድማማችነትን እና ቤተሰባዊነትን መፍጠር መቻል ነው፡፡

በዚህም የእግር ኳስ ጨዋታው በዲያስፖራው ማህበረሰብና በአመራሩ መካከል ያለውን ግንኙነት ማጠናከር ነው፡፡ ይህ ከሆነ በክልሉ ባሉት የልማት ስራዎች በጋራ በመሳተፍ ያለውን ፈጣን ዕድገት በማስቀጠል ዋነኛ ጠላታችን የሆነውን ድህነት ከመሠረቱ መናድ ያስችለናል ብለዋል፡፡

የክልሉ ወጣቶችና ስፖርት ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ አቶ ባዘዘው ጫኔ በበኩላቸው ይህ ጨዋታ የአንድነት፣ የወዳጅነትና የአብሮነት መገለጫ ነው፡፡

በመሆኑም ዲያስፖራውና አመራሩ በጋራ በመሆን ክልላቸውን ለመገንባት የድርሻቸውን ለመወጣት የሚያስችላቸውን ቃል ኪዳን የሚገቡበት ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የጨዋታውን መዝጊያ አስመልክቶ ንግግር ያደረጉት የፌዴሬሽን ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ የተከበሩት አቶ ያለው አባተ ያሉብንን አገራዊ ችግሮች በጋራ መወያየትና በጋራ መፍታት የጨዋታው ተቀዳሚ ዓላማ ነው፡፡ በመሆኑም ይህን ድምር ግንኙነታችንን ይበልጥ ለማጠናከር የዲያስፖራውን ቀን ሁሌም በየዓመቱ በደመቀ ሁኔታ እንዘክረዋለን፡፡

ጨዋታው አዝናኝ ከመሆኑም በላይ አስተማሪነቱ የጐላ በመሆኑ ዲያስፖራው ላደረገው ተሳትፎ ሊመሰገን ይገባል ብለዋል፡፡

በጨዋታው አብላጫ ውጤት ላስመዘገበው የዲያስፖራ ቡድን የወርቅ ዋንጫ የአመራሩ ቡድን ደግሞ ባሳየው ስፖርታዊ ጨዋነት የፀባይ የወርቅ ዋንጫ ተሸልመዋል፡፡

መረጃው የአማራ ክልል መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ነው

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy