የ2008 ዓ/ም ሀገር አቀፍ የወጣቶች የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ዛሬ በይፋ ተጀመረ። “እኛ ወጣቶች የተጀመረውን የህዳሴ ጉዞ በእውቀታችን እና ፕሮግራሙን በይፋ ያስጀመሩት የኢፌድሪ ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ደመቀ መኮንን ሲሆኑ በመክፈቻ ንግግራቸውም የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ዜጎች በራሳቸው ተነሳሽነት እና ውስጣቸው ከሚሰማቸው ሰብአዊ አመለካከት ተነስተው ለሚኖሩበት ማህበረሰብ ልማት እና ለአካባቢ ደህንነት ነፃ ግዚያቸውን፣ገንዘባቸውን፣እውቀታቸው እና በጎ አመለካከታቸውን ለሀገር ልማት የሚያውሉበት ጠቃሚ መድረክ መሆኑን በመግለፅ ወጣቶችም ከማህበረሰባቸው ጠቃሚ ባህላዊ እሴቶች የሚቀስሙበት እንደሆነ እና መርሀ ግብሩ በስኬት እንዲጠናቀቅ መንግስት በየደረጃው ድጋፍነሰ ክትትል እንደሚያደርግ ተናግረዋል። የኢፌድሪ ወጣቶች እና ስፖርት ሚንስቴር ሚንስትሩ አቶ ሬድዋን ሁሴን በበኩላቸው ወጣቶች ያሉባቸውን ማህበረሰባዊ ሀላፊነት በተግባር ለመወጣት የሚያስችላቸው ምቹ ሁኔታ በመፍጠር የወጣቶች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት መርሀ ግብር በመዘርጋት በበጋ እና በክረምት ወራት የወጣቶች ንቅናቄ ማረጋገጥ በኢኮኖምያዊ እና ማህበራዊ ልማት በርካታ ውጤት ማስመዝገብ መቻሉን በመግለፅ በአሁኑ ወቅት ሀገራችን የመጀመርያውን የእድገትና የትራንስፎርሜሽን እቅድ በማጠናቀቅ የሁለተኛውን የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ለማሳካት ርብርብ እያደረግን ባለበት ወቅት በመሆኑ ለእቅዱ ስኬታማነት ወጣቱ በቀጣይ የክረምት ወራት የሚያከናውናቸው የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶች የበኩሉን አስተዋፅኦ ሊያበረክት ይገባል ብለዋለ።
የዘንድሮው ሀገር አቀፍ የወጣቶች የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ከ 14 በላይ በሆኑ የተለያዩ አገልግሎቶች ከ12 ሚልየን በላይ ወጣቶች ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።