Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ኢትዮጵያ በልማት እየገሰገሰች ነው ፡- ጠ/ሚ/ር ቤንያሚን ኔታንያሁ

0 386

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ኢትዮጵያ በልማት እየገሰገሰች ነው ፡- ጠ/ሚ/ር ቤንያሚን ኔታንያሁ

ሰኔ 30፣ 2008

ኢትዮጵያ በልማት እየገሰገሰች መሆኗን የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚንስተር ቤንያሚን ኔታንያሁ አስታወቁ፡፡

 

ጠቅላይ ሚንስትሩ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በመገኘት ንግግር አድርገዋል፡፡ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ጉብኝት ያደረጉት ጠቅላይ ሚንስትሩ ኢትዮጵያም በልማት እየገሰገሰች ነው ብለዋል፡፡

እስራኤል በግብርና፣ በሃይል፣ በሳይንስ እና በጤና ዘርፍ ኢትዮጵያን ለመርዳት ዝግጁ መሆኗን ሀገሪቱ ጠቅላይ ሚንስተር ኔታንያሁ አስታወቀዋል፡፡

ኢትዮጵያን በመጎብኘት የመጀመሪያው ጠቅላይ ሚንስትር በመሆኔ ደስተኛ ነኝ ያሉት ጠቅላይ ሚንስትሩ ከወዲሁ በቀጣይ ኢትዮጵያን ስለመገብኘት እያሰብኩ ነው ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ እና የእስራኤል ትስስር ዘመናትን የተሻገረ መሆኑን የጠቆሙት ጠቅላይ ሚንስትሩ ኢትዮጵያ በእስራኤል ልብ ውስጥ አለች፡፡ እስራኤልም ኢትዮጵያ ልብ ውስጥ አለች ሲሉ አስታውቀዋል፡፡

ኢትዮጵያና እስራኤል ካላቸው የቆየ ታሪካዊ ግንኙነት በተጨማሪ ሀገራቱ ነጻነታቸውን ለማሰከበር ያደረጉት ትግልም ያመሳስላቸዋል ብለዋል፡፡  ከዚህ በተጨማሪ ሁለቱም ሀገራት ብዝሃነትን የማስተናገድ እና ሀገርን የመገንባት ጉዳይ እንደሚያመሳስላቸው ተናግረዋል፡፡

በአፍሪካ ጉብኝታቸው ሽብርተኝነትን ለማስወገድ መሰራት ስላለበት ጉዳይ መነጋገራቸውን ያስታወቁት ጠቅላይ ሚንስትር ኔታንያሁ አሸባሪዎችን በጋራ አንድ ሆነን ልንዋጋቸው ይጋባል ብለዋል፡፡ በሽብርተኝነት ላይ አብሮ መስራት በፍጥነት ውጤታማ እንድንሆን ያግዘናል ሲሉ አስታውቀዋል፡፡

የኢትዮጵያንም ሆነ የአፍሪካን እምቅ ሃይል ሳይ ኩራት ይሰማኛል ያሉት ጠቅላይ ሚንስትሩ ከጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ጋር ውጤታማ ውይይት አድርገናል ብለዋል፡፡

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አባዱላ ገመዳ በበኩላቸው እስራኤል በግብርና በሳይንስና ቴክኖሎጂ ያላት ተሞክሮ እ.አ.አ በ2025 መካከለኛ ገቢ ያላት ሀገር ለመገንባት ላለን አላማ ትልቅ ጠቀሜታ አለው ብለዋል፡፡

የሀገራቱ ግንኙነት እንዲጠናከር ልንረባረብ ይገባናል ያሉት አፈጉባኤው እስራኤላዊያን በኢንዱስትሪ እና በዘመናዊ ግብርና መሳተፍ የሀገራቱን ግንኙነቱ ያጠናክረዋል ሲሉ አስታውዋል፡፡

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy