NEWS

በሃገሪቱ የልማትና ኢንቨስትመንት ስራዎች ላይ ለመሳተፍ የኪራይ ሰብሳቢነት ችግር ማነቆ ሆኖብናል – የዳያስፖራ አባላት

By Admin

July 30, 2016

በሃገራችን መጥተን በልማትና በኢንቨስትመንት ስራዎች ላይ ለመሳተፍ የኪራይ ሰብሳቢነት ችግር ማነቆ ሆኖብናል ሲሉ የዳያስፖራ አባላት ተናገሩ።

የዳያስፖራ አባላቱ በአማራ ክልል ባሉ የኢንቨስትመንት ሁኔታ አማራጮችና የጥረት ኮርፖሬት እንቅስቃሴ ዙሪያ ከሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ጋር ተወያይተዋል።

በባህር ዳር ከተማ እየተከበረ ባለው የክልሉ የዳያስፖራ ቀን በዓል አከባበር ላይ እየተሳተፉ ያሉ አባላት፥ በሃገሪቱ የተለያዩ ቦታዎች የሚያቀርቸቧውን የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች ያለምክንያት ውድቅ የሚያደርጉና የሚያጓትቱ የመንግስት ስራ አስፈጻሚዎች እናንዳሉ ተናግረዋል።

መንግስት ቅድመ ሁኔታዎችን አመቻችቶ ሃገራቸው መጥተው እንዲያለሙ ጥሪ እንደሚያቀርብላቸው የጠቀሱት አባላቱ፥ በርካታ ኢትጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶችን ይዘው እንደሚመጡ ይመጣሉ ብለዋል።

ይሁን እንጅ በመሬትትና መሬት ነክ ጉዳዮች በኢንቨስትመንት ፈቃድ አሰጣጥና የግንባታ ስራ ላይ ችግር እንደሚገጥማቸው አንስተዋል።

አንዳንድ የኪራይ ሰብሳቢ አመለካከት ያላቸው የስራ አስፈጻሚ አካላት፥ ቀላል የማይባል ገንዘብ በይፋ ከመጠየቅ እስከ የመኖሪያ ቤትና ተሽከርካሪ እስከማስገዛት መድረሳቸውንም ያነሳሉ።

በዚህም ዳያስፖራው እቅዱን እንዳይፈጽምና ተሰላችቶ ወደ መጣበት እንዲመለስ እየሆነም ነው ያሉት።

በቀጣይ ይህ የሚፈታ ከሆነ ዳያስፖራው በትውልድ ሃገሩ ለማልማት ፍላጎት እንዳለውም በነበረው ውይይት ላይ ገልጸዋል።

የዳያስፖራ አባላቱ በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ ከሚመለከታቸው የመንግሰት አካላት ጋር የሚያደርጉት ውይይት ቀጥሎ እየተካሄደ ነው።