Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በዞኑ የኢንቨስትመንት አመራጮች ላይ ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆኑ ጥሪ ቀረበ

0 1,025

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በዞኑ የኢንቨስትመንት አመራጮች ላይ ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆኑ ጥሪ ቀረበ

በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በዞኑ የኢንቨስትመንት አመራጮች ላይ ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆኑ በአማራ ክልል የሰሜን ሸዋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ጥሪ አቀረቡ፡፡

ከተለያዩ ሀገራት የመጡ የዲያስፖራ አባላት የዞኑን የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴዎች ትናንት ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።

የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ግርማ የሽጥላ በጉብኝቱ ወቅት እንደገለጹት ባለፉት ዓመታት የሰሜን ሸዋን ህዝብ ልማት ለማፋጠን የተደረገውን ጥረት በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በመደገፍ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርገዋል፡፡

በዞኑ እስካሁን 69 የዲያስፖራ አባላት በተለያዩ የኢንዱስትሪ ልማት መስኮች ተሳትፈው በፈጠሩት የስራ እድል ወጣቶች ፣ሴቶችና አርሶ አደሮች ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡

በዞኑ የኢንቨስትመንት አማራጮች ላይ ተሳታፊና ተጠቃሚ ለመሆን ምቹ ሁኔታዎች እንዳሉም ጠቁመዋል፡፡

በጉብኝቱ የተሳተፉት የዲያስፖራ አባላት ወደ መጡበት ሲመለሱ እውነታውን ተገንዝበው በሀገሪቱ ያሉትን ተጨባጭ ለውጦች በማስተዋወቅ የድርሻቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።

የደብረ ብርሃን ከተማ ከንቲባ ታገል አምሳሉ በበኩላቸው ባለፉት አመታት 740 ሚሊዮን ብር ካፒታል ያስመዘገቡ የዲያስፖራ አባላት 31 ሄክታር መሬት ላይ 128 ኢንዱስትሪዎች መገንባታቸውን ተናግረዋል፡፡

በዚህም ራሳቸውንና ወገናቸውን ተጠቃሚ እያደረጉ መሆናቸውን ጠቁመው በቀጣይ ወደ ከተማው ለሚመጡና ባሉት የኢንቨስትመንት አማራጮች ላይ ለሚሳተፉ ትውልደ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያን ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት በቴክኖሎጂ የተደገፈ አሰራር መዘርጋቱን ገልጸዋል፡፡

ከዲያስፖራ አባላት መካከል የእንግሊዝ ዜግነት ያላቸው ትውልደ ኢትዮጵያዊዋ ወይዘሮ ትዕግስት አባቡ በሰጡት አስተያየት ” በሀገሪቱ የተመዘገበውን የልማትና የኢኮኖሚ እድገት ተዘዋውሬ በማየቴ ደስተኛ ነኝ “ብለዋል።

በጉብኝት ወቅት በተደረገላቸው ገለፃ በቀጣይ ጓደኞቻቸውንና ሌሎች ባለሀብቶችን በማስተባበር ለመስራት ተነሳሽነት እንደፈጠረባቸውም ገልጸዋል፡፡

ከደቡብ አፍሪካ ጁሃንስበርግ የመጡት ትውልደ ኢትዮጵያዊው አቶ መሰለ አያሌው በበኩላቸው ” የሀገሬ ወቅታዊና ተጨባጭ ሁኔታ መመልከት በመቻሌ ተደስቻለሁ “ብለዋል፡፡

በጉብኝታቸው ወቅት የተመለከቱት የኢኮኖሚ እድገት የመንግስት ድርሻ ከፍተኛ መሆኑን መገንዛብ እንደቻሉ ተናግረው ወደ መጡበት ሲመለሱም “የህዝብ ግንኙነት ስራን በማጠናከር ባለሀብቶች ወደ ኢትዮጵያ መጥተው እንዲያለሙ የበኩሌን እወጣለሁ”ብለዋል።

የዲያስፖራ አባላቱ በዞኑ ሀገረ ማሪያም ወረዳ ቱለፋ ቀበሌ በአንድ የውጭ ባለሀብት የተገነባውን የፕላስቲክ ማምረቻ፣ የአበሻ ቢራና የደብረብርሃን እንጨት ማቀነባበሪያ ፋብሪካን ጎብኝተዋል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy