Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

በጉልበታችን ከዳር ለማድረስ እንተጋለን” በሚል መሪ ቃል የ2008 ዓ/ም ሀገር አቀፍ የወጣቶች የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ዛሬ በይፋ ተጀምሯል።

0 613

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የ2008 ዓ/ም ሀገር አቀፍ የወጣቶች የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ዛሬ በይፋ ተጀመረ። “እኛ ወጣቶች የተጀመረውን የህዳሴ ጉዞ በእውቀታችን እና 13695165_1755363781404807_1751217692_nፕሮግራሙን በይፋ ያስጀመሩት የኢፌድሪ ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ደመቀ መኮንን ሲሆኑ በመክፈቻ ንግግራቸውም የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ዜጎች በራሳቸው ተነሳሽነት እና ውስጣቸው ከሚሰማቸው ሰብአዊ አመለካከት ተነስተው ለሚኖሩበት ማህበረሰብ ልማት እና ለአካባቢ ደህንነት ነፃ ግዚያቸውን፣ገንዘባቸውን፣እውቀታቸው እና በጎ አመለካከታቸውን ለሀገር ልማት የሚያውሉበት ጠቃሚ መድረክ መሆኑን በመግለፅ ወጣቶችም ከማህበረሰባቸው ጠቃሚ ባህላዊ እሴቶች የሚቀስሙበት እንደሆነ እና መርሀ ግብሩ በስኬት እንዲጠናቀቅ መንግስት በየደረጃው ድጋፍነሰ ክትትል እንደሚያደርግ ተናግረዋል። የኢፌድሪ ወጣቶች እና ስፖርት ሚንስቴር ሚንስትሩ አቶ ሬድዋን ሁሴን በበኩላቸው ወጣቶች ያሉባቸውን ማህበረሰባዊ ሀላፊነት በተግባር ለመወጣት የሚያስችላቸው ምቹ ሁኔታ በመፍጠር የወጣቶች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት መርሀ ግብር በመዘርጋት በበጋ እና በክረምት ወራት የወጣቶች ንቅናቄ ማረጋገጥ በኢኮኖምያዊ እና ማህበራዊ ልማት በርካታ ውጤት ማስመዝገብ መቻሉን በመግለፅ በአሁኑ ወቅት ሀገራችን የመጀመርያውን የእድገትና የትራንስፎርሜሽን እቅድ በማጠናቀቅ የሁለተኛውን የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ለማሳካት ርብርብ እያደረግን ባለበት ወቅት በመሆኑ ለእቅዱ ስኬታማነት ወጣቱ በቀጣይ የክረምት ወራት የሚያከናውናቸው የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶች የበኩሉን አስተዋፅኦ ሊያበረክት ይገባል ብለዋለ።

የዘንድሮው ሀገር አቀፍ የወጣቶች የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ከ 14 በላይ በሆኑ የተለያዩ አገልግሎቶች ከ12 ሚልየን በላይ ወጣቶች ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy