Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

በ 5 ቢልየን ብር ወጪ የተገነባዉ የሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ በነገው እለት ይመረቃል።

0 1,266

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

በ 5 ቢልየን ብር ወጪ የተገነባዉ የሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ በነገው እለት ይመረቃል።
#የበለጸገች_ኢትዮጵያ **
የሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ በቀጣይ በሀገሪቱ ለሚገነቡ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ሞዴል እና ፈር ቀዳጅ ነው ። *የሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ኢኮኖሚያዊ ትሩፋቶች፣ √ በሁለት ፈረቃ ለ60 ሺህ ሰዎች የስራ እድል ይፈጥራል √1 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር የውጭ ምንዛሬ ገቢ ያስገኛል √ሀገሪቱ ባለፉት 50 ዓመታት ከጨርቃ ጨርቅ ኢንደሰትሪ ስታገኝ የነበርውን ገቢም በ10 እጥፍ እንዲጨምር ያደርጋል። √በፓርኩ ውስጥ ከጨርቃጨርቅ አምራቾች በተጨማሪ ሌሎች ደጋፊ አምራቾች የሚገቡ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ የቁልፍ፣ የክር እና የመሳሰሉ የግብዓት አምራቾች ይገኙበታል። √15 የውጭ ሀገራት እና 5 የሀገር ውስጥ አምራቾች ወደ ፓርኩ ገብተዋል። * ከነዚህም ውስጥ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከ1300 ዓመት በላይ የማምረት ልምድ ያለው የፒ ቢ ኤች ኩባንያ ፣ እንዲሁም በዘርፉ ከፍተኛ ልምድ ያላቸው ኤን.ኤች ኤም እና ቫኒቲ ፔይርም በፓርኩ ውስጥ ገብተዋል። √ፓርኩ የአንድ ማእከል አገልግሎት ለመስጠትም የተደራጀ ሲሆን የገቢዎች እና ጉሙሩክ ባለስልጣን፣ የሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ፣ ባንኮች እና ሌሎችም አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ፓርኩ ውስጥ ይገባሉ። √የሀይል አቅርቦት ችግሩን ለመፍታትም በፓርኩ የራሱ የሆነ የኤሌክትሪክ ሀይል ማከፋፈያ ጣቢያ ተገንብቶለታል ። √ ፓርኩ በአካባቢው የሚለቀቁ በካይ ነገሮች የለውም ይህ ደግሞ በአፍሪካ ካሉ ጥቂት ከአካባቢ ጋር ተስማሚ ፋብሪካዎች አንዱ ያደርገዋል። በጨርቃ ጨርቅ ዘርፍ ብቸኛው የሆነው ይህ ፓርክ የአስተዳደር ስራው ለተወሰነ ጊዜ በውጭ ሀገራት ኩባንያዎች የሚከናወን ሲሆን፥ በሂደት ግን ኢትዮጵያውያን የሚረከቡት ይሆናል። መረጃውን የሰጡንየኢንዱሰትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የቦርድ ሰብሳቢ እና የጠቅላይ ሚኒስትሩ ልዩ አማካሪ ዶክተር አርከበ እቁባይ ናቸው እናመሰግናለን!!!

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy