ባህርዳር ከትናንት በስቲያ የተጀመረውና በነገው እለት ይጠናቀቃል ተብሎ የሚጠበቀው ሀገር አቀፋ የአማራ ክልል የዳያስፖራ በአል በዛሬ ውሎው በክልሉ በመከናወን ላይ ስላለው የኢንቨስትመንት ስራ ሰፊ ገለፃ ተደርጓል።
#የበለጸገች_ኢትዮጵያ
ባህርዳር ከትናንት በስቲያ የተጀመረውና በነገው እለት ይጠናቀቃል ተብሎ የሚጠበቀው ሀገር አቀፋ የአማራ ክልል የዳያስፖራ በአል በዛሬ ውሎው በክልሉ በመከናወን ላይ ስላለው የኢንቨስትመንት ስራ ሰፊ ገለፃ ተደርጓል። የአማራ ክልል ኢኮኖሚ በዋናነት የተመሰረተው በግብርና ሲሆን ግብርናው 55.9% ኢንዱስትሪው 15.7% እና የአገልግሎት ዘርፉ 28.9% ይሸፍናል። በክልሉ በስፋት የኢኮኖሚ የሀብት ምንጭ ከሆኑት በግብርና ማለትም የእንስሳት ሀብት ልማት፣የንብ ሀብት ልማት፣አበባ አትክልትና እፀ ጣእም ልማት፣በማእድንና ኢነርጂ እና በቱሪዝም ዘርፉ ደፋፊ የሚባሉ ስራዎች የተሰሩ ሲሆን በነዚህ ሰፊ የልማት እና የኢንቨስትመንት ስራዎች የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ እንደተቻለ ተገልጿል። ከዚህ በተጨማሪ በክልሉ የሚገኙ የኢንቨስትመንት አማራጮች እና ምቹ ሁኔታዎች ቀርበዋል በዚህ መሰረት የእንስሳት ሀብት ልማት እና የእንስሳት ውጤቶች፣በሆቴልና ተሪዝም ልማት ዘርፎች በኮንስትራክሽን እና ግንባታ ዘርፍ ዋናዋናዎቹ ሲሆኑ በክልሉ አስተማማኝ ሰላምና ጠንካራ የፍትህ ስርአት፣የመንግስት የልማት ድርጅቶች ትኩረት በሚሰጥባቸውዘርፎች ከባለሀብቱ ጋር ለመስራት ዝግጁ መሆናቸው፣መንግስት ለዘርፉ የሰጠው ትኩረት ከፍተኛ መሆን ፣የመሰረተ ልማት አውታሮች በስፋት መሟላታቸው ክልሉን ለኢንቨስትመንት ምቹ እንደሚያደርገውም ተወስቷል። ከውይይቱ ቡኃላ ከተሳታፊዎች የተለያዩ ጥያቄዎች ተነስተዋል ከመስርያ ቦታ አሰጣጥ መጓተት፣እቃ ከውጭ ለማስገባት ግሞሩክ አካባቢ የሚስተዋሉ እንግልቶች በአጠቃላይ አገልግሎት አሰጣጡና የመልካም አስተዳደር ችግሮች ስራ ላይ እንቅፋት እንደፈጠረባቸው እንዲሁም በጎንደርና አካባቢው ስለሚነሱ ችግሮች እና ህገ ወጥ የሰዎች ዝውወርን ለመግታት በመንግስት በኩል ምን ለመስራት እንደታቀደ እና ስለችግሩ አፈታት ዙርያ የተለያዩ ሀሳቦችን አንስተዋል። በተነሱት ጥያቄና አስተያየቶች የተለያዩ የስራ ሀላፊዎች መልስ ሰጥተውበታል የተነሱት ችግሮች እንዳሉና ችግሩን ለመፍታት በጋራ መስራቱ ተመራጭ መሆኑ ተገልጿል። ለተጨማሪ መረጃ ቀጣዮን ቪድዮ ይመልከቱ