Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

አብዛኛውን የ”ስትሮክ” በሽታ መንስዔ መከላከል ይቻላል

0 2,297

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

አብዛኛውን የ”ስትሮክ” በሽታ መንስዔ መከላከል ይቻላል

በካናዳ ማክማስተር ዩኒቪርስቲ የስነ-ህዝብና ጤና ተቋም ከሰሞኑ በመካከላኛና ዝቅተኛ ገቢ ባላቸው አገራት ከፍተኛውን የሞትና የአካል ጉድለት በሚዳርገው “ስቶሮክ” በሽታ ላይ ያደረገው የጥናት ውጤት ይፋ አድርጓል፡፡ በአለማችን ከፍተኛ፣ መካከለኛና ዝቅተኛ ገቢ ባላቸው 26 ሺህ ሰዎች ላይ የተካሄደው ጥናት 90 በመቶ የሚሆነውን የ”ስትሮክ” በሽታ መከላከል እንደሚቻል ያመለክታል፡፡

በአመዛኙ በመካከለኛና ዝቅተኛ ገቢ ባላቸው አገራት የሚታየው “ስትሮክ” በድንገተኛ የአዕይምሮ ደም ዝውውር መቋረጥ የሚከሰት ሲሆን በማንኛውም ሰው ላይ ሊከሰት ይችላል፡፡ የ”ስትሮክ” በሽታ በሁለት ክፍሎች ይከፈላል፡፡ የመጀመሪያው “ischaemic stroke” እስካሚክ “ስትሮክ” በመባል የሚታወቀው ሲሆን 85 በመቶ የስትሮክ በሽታ ድርሻን ይዛል፡፡ እስከሚክ ስትሮክ በደም መርጋት የሚከሰት የ”ስትሮክ” በሽታ አይነት ነው፡፡ ሁለተኛው የ”ስትሮክ” አይነት “haemorrhagic stroke” ሄሞራጂክ ስትሮክ በመባል የሚታወቅ ሲሆን ቀሪውን 15 በመቶ የ”ስትሮክ” በሽታ ድርሻን ይዛል፡፡ ሄረሞራጂክ ስትሮክ በአዕምሮ ደም መፍሰስ የሚከሰት የ”ስትሮክ” በሽታ አይነት መሆኑን የሳይንስ ዴይሊ ዘገባ ያስረዳል፡፡

በጥናቱ መሰረት ከታች የተጠቀሱ 10 የ”ስትሮክ” በሽታ መከላከያ ዘዴዎችን በመጠቀም ከ10 በ”ስትሮክ” በሽታ ከሚሞቱ ሰዎች የ9ኙን ህይወት ማትረፍ ይቻላል፡፡

1.የደም ግፊት በሽታን በመከላከል 48 %
2.የአካል ብቃት አንቅስቃሴን አዘውትሮ በመስራት 36 %
3.አመጋገብን በማስተካከል 19 %
4.ሲጋራን በማቆም 12 %
5.የልብ በሽታን በመከላከል 9 %
6.የስኳር በሽታን በመከላከል 4 %
7.የአልኮል መጠጥን በማቆም 6 %
8.አለአስፈላጊ ጭንቀትን በማስወገድ 6 %
9.ኮልስተሮል ያለባቸውን ምግቦች በማቆም 27 %
10 ከላይ የተጠቀሱ የ”ስትሮክ” በሽታ መከላከያ መንገዶች በጥቅሉ 91 በመቶ የስትሮክ በሽታን መከላከል ይቻላል፡፡

EBC's photo.

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy