Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

አንድ ቢሊዮን ዶላር የሚያስገባው የኢንዱስትሪ ፓርክ ሃምሌ 6 ይመረቃል

0 489

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

አንድ ቢሊዮን ዶላር የሚያስገባው የኢንዱስትሪ ፓርክ ሃምሌ 6 ይመረቃል

በዓመት አንድ ቢሊዮን ዶላር የሚያስገባው የሃዋሳ ጨርቃጨርቅና አልባሳት ኢንዱስትሪ ፓርክ በመጪው ረቡዕ ይመረቃል፡፡

 

ፓርኩ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀዳሚ የአምራች ኢንዱስትሪ ማዕክል ለመሆን ላስቀመጠችው ግብ ስኬታማነት ፈር ቀዳጅ መሆኑን የጠቅላይ ሚንስትሩ ልዩ አማካሪ ሚንስትር ዶ/ር አርከበ እቁባይ ገለቷል፡፡

በ300 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ ያረፈው የሃዋሳ የጨርቃጨርቅና አልባሳት ኢንዱስትሪ ፓርክ በ250 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ወጪ ነው የተገነባው፡፡

በኢንዱስትሪ ፓርኩ የሚመረት ምርት ሙሉ ለሙሉ ለውጭ ገበያ የሚቀርብ ሲሆን በዓመት አንድ ቢሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሪ እንደሚያስገኝ ይጠበቃል፡፡

ለ60 ሺህ ሰዎች የስራ እድል ይፈጥራል የተባለው የኢንዱስትሪ ፓርኩ ግንባታ ሙሉ ለሙሉ የተጠናቀቀ ሲሆን ሃምሌ 6/2008 ስራ እንደሚጀምር የጠቅላይ ሚንስትሩ ልዩ አማካሪና የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የቦርድ ሰብሳቢ ዶ/ር አርከበ እቁባይ ገልጸዋል፡፡

ከኢንዱስትሪ ፓርኩ ግንባታ በርካታ ልምድ መገኘቱንና ሀገሪቱ በአፍሪካ ቀንድ የአምራች ኢንዱስትሪ ማዕከል ለመሆን ላስቀመጠችው ግብ ፈር ቀዳጅ መሆኑን ነው የተናገሩት፡፡

ወደ ፓርኩ የሚገቡ ስድስት የሀገር ውስጥና 15 የውጭ ሀገር ኩባንያዎቸ መለየታቸው ታውቋል፡፡

የውጭ ሀገር ኩባንያዎቹ በዘርፉ ትልቅ ስም ያላቸው መሆኑን የኢንቨስትንት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ፍጹም አረጋ ተናግረዋል፡፡

ወደ ኢንዱስትሪ ፓርኩ ለሚገቡ የሃገር ውስጥ ባለሃብቶች ከ85 በመቶ የኢንቨስትመንት ብድር አንስቶ የስልጠናና የገበያ ትስስር መመቻቸቱ ታውቋል፡፡

በኢንዱስትሪ ፓርኩ ለሚሰሩ ኢትዮጵያዊያን የተለያዩ ስልጠናዎች እንደሚሰጡ የኢንዱስትሪ ሚንስትር ዲኤታ አቶ ታደሠ ሃይሌ ገልጸዋል፡፡

ሪፖርተር፡- ጌታቸው ባልቻ

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy