#የበለጸገች_ኢትዮጵያ #የኢትዮጵያ_የዳያስፖራ_ቀን በክልል ደረጃ ከሐምሌ 21 _ 24/2008 ዓ.ም ባህር ዳር ከተማ እንዲሁም በሀገር አቀፍ ደረጃ ከሐምሌ 25 _ 26 2008 ዓ/ም ለሚከበረው የዳያስፖራ በዓል ተሳታፊዎች የዳያስፖራ አባላት ወደ ሃገር ውስጥ መግባት ጀምረዋል። በአማራ ክልል ባህር ዳር ከተማ የሚከበረውን የዳያስፖራ በዓል ለማስተናገድ የሚያስችለው የቅድመ ዝግጅት ስራ መጠናቀቁም ተገልጿል። በዓሉን በተለያዩ ዝግጅቶች የሚከበር ሲሆን ተሳታፊ ዳያስፖራዎቹ ከበዓሉ በፊት የተከናወኑ የልማት ስራዎች ይጎበኛሉ፣ በሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ፣ በኢንቨስትመንት አማራጮችና በሌሎች የልማት ጉዳዮች ዙሪያ የፓናል ውይይት ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል። ከዚህ በተጨማሪ ተሳታፊ የዳያስፖራ አባላት በሚመርጧቸው ዞኖችና ከተማ አስተዳደሮች የኢንቨስትመንት መሬት ተመቻችቷል። በበዓሉ ላይ ከ3 ሺ በላይ ዳያስፖራዎች ይሳተፉሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን እስከአሁን 2400 የሚሆኑት ተመዝግበው ወደ ሃገር ውስጥ መግባት መጀመራቸውም ታውቋል።
- Comments
- Facebook Comments
Follow Us @ethiopiaprosperous
porn videos