Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ህብረተሰቡ ፀረ ሰላም እንቅስቃሴዎችን በመከላከል ረገድ እገዛ እያደረገ ነው – የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን

0 1,283

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ህብረተሰቡ ፀረ ሰላም እንቅስቃሴዎችን በመከላከል ረገድ እገዛ እያደረገ ነው – የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን

ህብረተሰቡ ፀረ ሰላም እንቅስቃሴዎችን በመከላከል ረገድ እገዛ እያደረገ ነው - የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን

ህብረተሰቡ በአንዳንድ አካባቢዎች የተስተዋሉ ፀረ ሰላም እንቅስቃሴዎችን በመከላከል እና ከእኩይ ተግባራቸው እንዲቆጠቡ በማድረጉ ረገድ ከፍተኛ እገዛ እያደረገ መሆኑን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

ህገ መንግስቱ ማንኛውም ዜጋ ጥያቄዎችን በተናጠልም ሆነ በህብረት የሚያቀርብበት አሰራርን አስቀምጧል፤ በዚህ አግባብም በተለያየ ጊዜ ህግን ተከትለው የሚነሱ ጥያቄዎች ተገቢውን የጸጥታ ከለላ አግኝተው ሲስተናገዱ ቆይተዋል።

በቅርቡ በኦሮሚያ እና በአማራ አንዳንድ አካባቢዎች የተከሰተው ድርጊት ግን ፍጹም ህገወጥ ነው ብሏል የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን።

ኮሚሽነር ጀኔራል አሰፋ አብዩ ዛሬ በሰጡት መግለጫ፥ 99 በመቶ የሚሆኑት በህገወጥ ሰልፉ የተሳተፉ ዜጎች በቂ ግንዛቤ ሳይኖራቸው በቦታው የተገኙ ናቸው ብለዋል።

ከዚህ አንጻርም የህብረተሰቡን የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ጥቂት ፀረ ሰላም ሃይሎች በህብረተሰቡ ውስጥ ሰርገው በመግባት ህገ መንግስታዊ ስርአቱን የሚፃረሩ ድርጊቶችን ሲፈፅሙ ተስተውለዋል ነው ያሉት።

በህገወጥ ሰልፎቹ የሃገሪቱን ሰንደቅ አላማ እስከ መቀየር እና ብሄርን ከብሄር የሚያጋጩ ቅስቀሳዎች መደረጋቸውን ጠቅሰው፥ ድርጊቱ ፈፅሞ ህዝባዊ መሰረት የሌለው እና ኢትዮጵያዊ እሴትን የሚያጎድፍ በመሆኑ ተቀባይነት የለውም ብለዋል።

ህብረተሰቡም ይህን በመረዳቱ በተለያዩ አካባቢዎች የተስተዋሉ ፀረ ሰላም እንቅስቃሴዎች እና እኩይ ተግባርን በመግታት እና ከዚህ እኩይ ተግባራቸው እንዲታቀቡ በማድረጉ ረገድ ከፍተኛ እገዛ እያደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

ኮሚሽነሩ ህብረተሰቡ ላሳየው ትብብር እና ጥረትም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

በተስተዋሉ ሁከቶች እና ግጭቶች የሃገሪቱን ሰላም እና የልማት እንቅስቃሴዎችን ለማስተጓጎል መቀመጫቸውን በውጭ ሃገራት ያደረጉ የጥፋት ሃይሎች ከፍተኛ እንቅስቃሴ ማድረጋቸውንም ገልጸዋል።

በዚህ ህገ ወጥ ድርጊትም የንፁሃን ዜጎች ህይወት መጥፋቱን ጠቁመው፥ ከፍተኛ ንብረት መውደሙንም ነው ኮሚሽነር ጀኔራሉ የተናገሩት።

በአሁኑ ሰአትም ፀረ ሰላም ሃይሎች የሃገሪቱን ሰላም ለማወክ እና እየተካሄደ ያለውን ልማት ለማደናቀፍ ከመቼውም ጊዜ በላይ እየተጉ በመሆናቸው፥ ህብረተሰቡ ይህን ጠንቅቆ በመረዳት ከመቸውም ጊዜ በላይ ነቅቶ ሊጠብቃቸው እንደሚገባ አሳስበዋል።

ፀረ ህገ መንግስታዊ እንቅስቃሴዎች ላይ የጥቂት ግለሰቦች እጅ ነበር ያሉት ኮሚሽነር ጀኔራሉ፥ በቂ ግንዛቤ ሳይኖራቸው በቦታው የተገኙትን የመለየት ስራ መከናወኑንም አንስተዋል።

ህገወጥ መሳሪያዎችን በመጠቀም በመሰረተ ልማቶች እና በግለሰቦች ላይ ጉዳት ያደረሱ ግለሰቦችን በህግ ተጠያቂ የማድረጉ እና ህጋዊ እርምጃ የመውሰዱ ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላልም ነው ያሉት።

ከዚህ ጋር ተያይዞም በሁከቱ በቀጥታ ተጠያቂ የሚሆኑ የተለያዩ አካላትም ለህዝቡ ይፋ እንደሚደረጉም አስረድተዋል።

በቀጣይም ህብረተሰቡ ከሰላሙ ተጠቃሚው እራሱ መሆኑን በመረዳት ከፀጥታ ሃይሉ ጋር በመቀናጅት የሃገሪቱን ሰላም ለማስጠበቅ ከመቸውም በላይ እንዲረባረብ ኮሚሽነር ጀኔራሉ ጥሪ አቅርበዋል።

 
በተመስገን እንዳለ

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy