Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

“በብሄር አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ መከካል የሃሳብ ልዩነት ተፈጥሯል የተባለው ወሬም ከእውነት የራቀና መሰረተ ቢስ ነው”።

0 430

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

“በብሄር አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ መከካል የሃሳብ ልዩነት ተፈጥሯል የተባለው ወሬም ከእውነት የራቀና መሰረተ ቢስ ነው”።
የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የብአዴን ሊቀመንበር አቶ ደመቀ መኮንን ዛሬ በባህርዳር ከተማ በሰጡት መግለጫ

ህዝቡ እያነሳቸው ላሉ ጥያቄዎች ፈጣን ምላሽ በመስጠት በሁሉም ዘርፍ እየተመዘገበ ያለው ፈጣን ልማትና ዕድገት ግለቱን እንደጠበቀ ተጠናከሮ እንዲቀጥል ብአዴን የመሪነት ሚናውን በላቀ ብቃት እንደሚወጣ የድርጅቱ ሊቀመንበር አቶ ደመቀ መኮንን አስታወቁ።
በብሄር አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ መከካል የሃሳብ ልዩነት ተፈጥሯል የተባለው ወሬም ከእውነት የራቀና መሰረተ ቢስ መሆኑንም ገልጸዋል።
የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የብአዴን ሊቀመንበር አቶ ደመቀ መኮንን ዛሬ በባህርዳር ከተማ በሰጡት መግለጫ እንደገለጹት፥ በአማራ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች በተከሰተው ግጭት ሳቢያ በጠፋው የሰው ህይወትና በወደመው ንብረት ብአዴን አዝኗል።
በብአዴን አመራር በክልሉ ባለፉት ዓመታት በተከናወኑ ዘርፈ ብዙ የልማት ሥራዎች ክልሉ ይታወቅበት ከነበረው ድህነትና ኋላቀርነት በማላቀቅ ወደ ተሻለ የእድገት ከፍታ እንዲወጣና ህዝቡም ከልማቱ ተጠቃሚ እንዲሆን ማድረግ ተችሏል ብለዋል።
በክልሉ አንዳንድ አካባቢዎች በህገ ወጥ መንገድ በተካሄዱ ሰልፎች የሰው ህይወት ጠፍቷል፤ ንብረት መድሟል ያሉት አቶ ደመቀ፣ ይህ ደግሞ የሰላም ወዳዱ የአማራ ክልል ህዝብ መገለጫ ባህሪ አይደለም ብለዋል።
የአማራ ክልል ህዝብ የዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታው አሁን ከደረሰበት ደረጃ እንዲደረስ በትጥቅ ትግል ሳይቀር ታላቅ መስዕዋት የከፈለ ባለ ታሪክ ህዝብ መሆኑንም ገልፀዋል።
ህዝቡ በተደራጀ አግባብ እያነሳቸው የሚገኙ የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ደረጃ በደረጃ ለማቃለል ብአዴን ከመቸውም ጊዜ በተሻለ ሁኔታ ብርቱ ጥረት እያደረገ ነውም ብለዋል።
ህዝብና መንግሥት ተቀራርበውና ተባብረው በመስራት የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለማቃለል እያደረጉት ያለውን ጥረት በበለጠ አጠናክረው እንደሚቀጥሉም አቶ ደመቀ ተናግረዋል።
በክልሉ አንዳንድ አከባቢዎች ሰሞኑን የተካሄዱ ህገ-ወጥ ሰልፎች ተቀባይነት የሌላቸውና ፀረ-ሰላምና ፀረ-ልማት ተልዕኮ ባነገቡ አካላት ግፊት የተፈጸሙ መሆናቸውን ህዝቡ ተገንዝቦ የአካባቢውን ሰላም ለመጠበቅ ነቅቶ መንቀሳቀስ እንዳለበት አስገንዝበዋል።
በተለይ መሰረተ-ቢስ ወሬዎችን በመንዛት ክልላዊና ሀገራዊ አጀንዳዎችን በማንሳት የህዝቡን ሰላም ለማወክና ልማቱን ለማደናቀፍ አልመው የሚንቀሳቀሱ ፀረ-ሰላምና ፀረ-ልማት ኃይሎችን ህዝቡ በፅናት እንዲታገቸውም አሳስበዋል።
የድርጅቱ ሊቀመንበር በመግለጫቸው እንዳስገነዘቡት ሁከትና ብጥብጥ ለአማራ ክልል ህዝብ የሚጠቅም ሳይሆን በውስን የሕዝብ ሀብት የተገነቡ የመሰረተ ልማት አውታሮችን የሚያፈራርስና የሚያወድም እኩይ ተግባር ነው።
ህዝብ ለመንግሥት የሚያቀርባቸው ጥያቄዎች በተደራጀ አግባብ ህግንና ስርዓትን መሰረት አድርጎ መሆን እንዳለበት ጠቁመው፣ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት ሕዝባዊ ውይይቶች በየደረጃው እየተካሄዱ መሆናቸውን አስታውቀዋል።
መንግሥትም በሀገሪቱ የተጀመረው የሰላም፣ የልማትና የዲሞክራሲ ሥርዓትን የማጠናከርና የህግ የበላይነትን የማረጋገጥ ሥራውን ከህዝብ ጋር ሆኖ አጠናከሮ ይቀጥላል ብለዋል።
በብሄር አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ/ብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ መከካል የሃሳብ መከፋፈል ተፈጥሯል የተባለው ወሬም ከእውነት የራቀና የተለመደ የማደናገሪያ መሰረተ-ቢስ አሉባልታ እንደሆነም ሊቀመንበሩ ተናግረዋል።
ብአዴን የካበተ የመምራት ልምድና ብቃት ያለው፣ በህግና ሥርዓት የሚመራ፣ የአጭር፣ የመካከለኛና የረጅም ጊዜ ዕቅድና መርሃ ግብሮችን ነድፎ የሚተገብር፣ የሕዝቡን ሁለንተናዊ ጥቅም የሚያስቀድምና የድርጅት መርህን ተከትሎ እየሰራ ያለ ጠንካራ ድርጅት ነውም ብለዋል።
ብአዴን በየወቅቱ ለሚነሱ ጉዳዮች የበሰለና የነጠረ የውስጥ ድርጅት ትግል እያካሄደ፣ የተለያዩ ሃሳቦች በነጻነት እንዲንሸራሸሩ እያደረገ ወደ አንድ ወሳኝ ድምዳሜ የሚደርስ በበሳል ዲሲፕሊን የሚመራ የሕዝብ ድርጀት ነው።
መሆኑም በክልሉ አንዳንድ አካባቢዎች ሰሞኑን በተከሰተው ሁከትና ግርግር ማዕከላዊ ኮሚቴው ተከፋፍሏል የሚባለው ወሬ ከእውነት የራቀ መሆኑን አቶ ደመቀ ተናግረዋል።
እንደዚህ አይነት መሰረተ-ቢስ ወሬዎች ለድርጅቱ አዲስ እንዳልሆኑና የነበሩ፣ ያሉ፣ ወደ ፊትም ሊነሱ እንደሚችሉ ጠቁመው፣ እውነታው ግን ሁሉም ጉዳይ በህግና በሥርዓት ብቻ የሚከናወን መሆኑን አረጋግጠዋል።
ብአዴን በየጊዜው ከድክመቱ ለመማርና ጉድለቱን ለማረም የተዘጋጅ ድርጅት መሆኑን የገለፁት አቶ ደመቀ፥ ህዝቡ ችግሮች ሲያጋጥሙት በውይይትና በመመካከር መፍትሄ ማበጀት እንደሚገባም ተናግረዋል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy