Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

አሜሪካ ለኢትዮጵያ ተጨማሪ የ35 ሚሊየን ዶላር የሰብዓዊ ድጋፍ አደረገች

0 474

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

አሜሪካ ለኢትዮጵያ ተጨማሪ የ35 ሚሊየን ዶላር የሰብዓዊ ድጋፍ አደረገች

አሜሪካ ለኢትዮጵያ ተጨማሪ የ35 ሚሊየን ዶላር የሰብዓዊ ድጋፍ አደረገች

ዩናይትድ ስቴትስ ኤል ኒኖ ባስከተለው ድርቅ ምክንያት ድጋፍ ለሚሹ ዜጎች የሚውል የተጨማሪ 35 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ድጋፍ አደረገች።

የአሜሪካ መንግስት ይፋ ያደረገው የሰብዓዊ እርዳታ በድርቁ ምክንያት የሰብዓዊ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ሰዎች ድጋፍ እያቀረቡ በሚገኙት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና በተለያዩ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች በኩል የሚደርስ ይሆናል።

ድጋፉ 6 ሺህ ሜትሪክ ቶን አልሚ ምግብን ያካተተ ሲሆን፥ በደርቁ ምክንያት ለተመጣጠነ ምግብ እጥረት ለተጋለጡ ዜጎች ይከፋፈላልም ነው ያለው የአሜሪካ ኤምባሲ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ።

የዩ ኤስ አይድ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ሌስሊ ሬድ፥ የዩናይትድ ስቴትስ መንግስት በድርቁ ምክንያት የተጎዱ ኢትዮጵያውያን ይህን አስቸጋሪ ጊዜ እንዲያልፉ ከጎናቸው መሆኑን አረጋግጠዋል።

ዩ ኤስ አይድ በድርቅ በተጎዱ አከባቢዎች ዘር በማቅረብ እና ገበሬዎች ከብቶቻቸውን እና ሌሎች ንብረቶቻቸውን እንዳይሸጡ እና ድርቁን ተቋቁመው በሁለት እግራቸው እንዲቆሙ የበኩሉን ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ነው የገለፀው።

የዩናይትድ ስቴትስ መንግስት ከፈረንጆቹ 2015 ጀምሮ ለኢትዮጵያ በአጠቃላይ የ774 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ድጋፍ አድርጓል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy