Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

በ11ኛው ዙር እጣ ያልወጣባቸው የ10/90 ቤቶች ለልማት ተነሺዎች ሊከራዩ ነው

0 1,422

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

በ11ኛው ዙር እጣ ያልወጣባቸው የ10/90 ቤቶች ለልማት ተነሺዎች ሊከራዩ ነው

በ11ኛው ዙር እጣ ያልወጣባቸው የ10/90 ቤቶች ለልማት ተነሺዎች ሊከራዩ ነው

በ11ኛው ዙር የጋራ መኖርያ ቤቶች እጣ ለእድለኞች ሙሉ በሙሉ ተላልፈው የተረፉ የ10/90 ቤቶች በልማት ለሚነሱ ነዋሪዎች በተመጣጣኝ ኪራይ ሊተላለፉ ነው።

በ10/90 የቤቶች ፕሮግራም ቁጠባቸውን ካቋረጡት ተመዝጋቢዎች ውጪ ለሁሉም ተደራሽ መሆናቸውን የአዲስ አበባ ቤቶች አስተዳደር ኤጀንሲ ስራ አስኪያጅ አቶ ሽመልስ ታምራት ተናግረዋል።

ከተማ አስተዳደሩ ከዚህ ቀደም የልማት ተነሽዎች እንደፍላጎታቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች አልያም የቀበሌ ቤቶችን እንዲመርጡ ይደረግ እንደነበር ያስታወሱት ስራ አስኪያጁ፥ አሁን ግን ኮንዶሚኒየም መግባት ለፈለጉና የመክፈል አቅም ለሌላቸው ተነሺዎች በተመጣጣኝ ዋጋ ቤቶቹ በኪራይ መልክ ይተላለፋሉ ብለዋል።

ኤጀንሲው ለመጀመሪያ ጊዜ በጋራ መኖሪያ ቤቶች ቅድሚያ የተሰጣቸውን አካል ጉዳተኞች ጨምሮ ለሴቶችና ለመንግስት ሰራተኞች በተሰጠው እድል 18 ሺህ 735 የቤት ተመዝጋቢዎች ተጠቃሚ መሆናቸውንም አመላክቷል።

በ10/90 የቤቶች ፕሮግራም 12 ሺህ 784 ነዋሪዎች በልዩ ሁኔታ እድሉን ሲያገኙ በ20/80 ፕሮግራም ደግሞ 5 ሺህ 951 ቤት ፈላጊዎች ቅድሚያ ተሰጥቷቸዋል፡፡

በዚህም ከ14 ሺህ በላይ ሴቶች፣ ከ700 በላይ አካል ጉዳተኞችና ከ3 ሺህ በላይ የመንግስት ሰራተኞች ተጠቃሚ መሆናቸውን ነው ኤጀንሲው ያስታወቀው።

ባሳለፍነው ሐምሌ 30 በወጣው 11ኛው ዙር የጋራ መኖሪያ ቤቶች እጣ ከ39 ሺህ በላይ ቤቶች ዕጣ መውጣቱ የሚታወስ ነው፡፡

በዕጣው ለሴቶች 30 በመቶ፣ ለመንግስት ሰራተኞች 20 በመቶ፤ ለአካል ጉዳተኞች ደግሞ 5 በመቶ ቅድሚያ ተሰጥቷል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy