Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ሀገራችን በመሠረቱ በትክክለኛ መንገድ ላይ እንዳለች እና እየተከተለች ያለችው አቅጣጫም እንከን እንደሌለው መሆኑን ለአፍታም መዘንጋት የለበትም፡

0 377

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

መሠረታዊ እና ስርነቀል ለውጥ እያስመዘገበ በሽግግር ምዕራፍ ላይ የሚገኝ ማንኛውንም ሀገር ሊገጥም የሚችል ጊዜያዊ ተግዳሮት ብቻ ነው የገጠመን እንጂ ልዩ ተዓምር በእኛ ላይ ብቻ የደረሰ ተደርጐ መታየት የለበትም፡፡ በዚህ ሽግግር ወቅት አስተማማኝ መሠረት በሁሉም መስክ መጣላችን መዘንጋት የለበትም፡፡ – ይኼ አስተማማኝ መሠረት በጊዜያዊ ችግሮች ወይም ንፋሳት የሚናወጥ አይደለም፡፡ የሚገጥሙን እና እየገጠመን ያለው ተግዳሮት ዋናው ምንጭ የዕድገት ደረጃችን ያወረዳቸው አዳዲስ ፍላጐት እና በአዳዲስ ፍላጐቱ መጠን በቂ አቅርቦት ማቅረብ አለመቻላችን ነው ፡፡ ይኼ ጉድለት የሚፈታው በቂ አቅርቦት ማሟላት የሚቻልበትን ዙሪያ መለስ ጥረት ማድረግ ይጠይቃል፡፡ – እንደተለመደው ይኼ ሁኔታ እጅግ የቆረጠና የጨከነ ብቁ አመራርን ይጠይቃል፡፡ ይኼ ፈተና በራሱ እንደትምህርት ቤት ሆኖ በሂደት ብቁ አመራር የሚፈራበት፣ ከፍተኛ የህዝብ ተሳትፎ የሚረጋገጥበት፣ የልማታዊ ባለሀብት ተሳትፎ የሚረጋገጥበት ይሆናል፡፡ – እስከ አሁን በነበሩን ሂደቶች ትልልቅ ፈተናዎች ሲለመፍታት ብዙ ጥረቶች እየተደረጉ አመርቂ ድሎች እየተመዘገቡ እዚህ ደርሰናል፡፡ አሁን የደረስንበት ደረጃም የራሱ የሆነ ልዩ ባህሪና ተግዳሮት እንዲሁም እድል ይዞ መምጣቱ አይቀርም፡፡ – በተለይም ዘመናትን ተሻግረው ከእኛ ጋር እየዘለቀ ያለው ትምክህተኛነት፣ ጠባብነትና ኪራይ ሰብሣቢነት አሁንም ተግዳሮት መሆኑ አይቀርም፡፡ – አሁንም እየገጠመን ያለውን ተግዳሮት በደንብ ካየነው ይሄ ኋላቀር አስተሳሰብ አሁንም የሥርዓታችን አደጋ መሆኑን ማየት ይቻላል፡፡ – አሁን እየገነባን ያለነው ስርዓት የእኩልነት የዴሞክራሲ፣ የብዛሃነት፣ የመቻቻል የመከባበር፣ በፈቃደኛነት ያለ የተመሠረተ አንድነት ግንባታ ሥርዓት መሆኑን ምልዓተ ህዝብ ያውቃል ያምናልም፡፡ – ሀገራችን በመሠረቱ በትክክለኛ መንገድ ላይ እንዳለች እና እየተከተለች ያለችው አቅጣጫም እንከን እንደሌlው መሆኑን ለአፍታም መዘንጋት የለበትም፡፡ – እዚህም እዛም አልፎ አልፎ የሚያግጠሙን ጉድለቶች ማንኛውም ታዳጊ ሀገር በተለይም መሠረታዊ የለውጥ ምዕራፍ ውስጥ የገባ ሀገር ሊያጋጥመው ከሚችል ተግዳሮት ወጭ ሌላ የተለየ ዱብ እዳ ከሰማይ የልወረደብን/ያልደረሰብን መሆኑ በውል ሊታወቅ ይገባል፡፡

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy