Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ውዝፍ የመሬት ሊዝ ክፍያ ጊፍት ሪል ስቴት እና የመንግስት መስሪያ ቤቶችን እያወዛገበ ነው

0 1,059

Get real time updates directly on you device, subscribe now.


የተጠተራቀመ ውዝፍ የመሬት ሊዝ ክፍያ ጊፍት ሪል ስቴት እና አራት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መስሪያ ቤቶችን እያወዛገበ ነው።

የጊፍት ቢዝነስ ግሩፕ ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ ገብረኢየሱስ ኢጋታ እንደሚናገሩት፥ ጊፍት ሪል ስቴት ከዛሬ አስር አመት በፊት በ99 አመት የሊዝ ኪራይ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሬት ወስዷል።

ሪል ስቴቱ በወሰደው መሬት ላይ በመቶዎች የሚቆጠሩ ቤቶችን ገንብቶ ለገዢዎች ስለማስረከቡም አቶ ገብረኢየሱስ ተናግረዋል።

ቤት ገዢዎቹም በተለያየ ጊዜ የገዙትን ቤት ቢረከቡም የገዙት ቤት የእነርሱ ስለመሆኑ ማረጋገጫ የሚሰጠው ካርታ ግን በእጃቸው የለም፤ ሪል ስቴቱ ቤቶችን ገንብቶ ካስረከበባቸው ሳይቶች ውስጥ ውሃ እና መብራት አለመኖሩንም ይናገራሉ።

ቤት ገዢዎቹ እነዚህ አገልግሎቶች በመንግስት በኩል ሊቀርቡ የሚገባቸው እና ማግኘት ያልቻልናቸው ናቸው በሚል አቤቱታቸውን አቅርበዋል።

አቶ ገብረኢየሱስ ጊፍት ሪል ስቴት እንደ ቤት አልሚ ለተገነቡት ቤቶች አስፈላጊው መሰረት ልማት እንዲሟላ ጠይቋል ይላሉ።

የየካ ክፍለ ከተማም የተናጠል ይዞታ ማረጋገጫ ካርታ መስጠትን ጨምሮ ሌሎች አገልግሎቶችን መስጠት አልችልም ሲል፥ ቤት አልሚው ጊፍት ሪል ስቴት እና ቤት ገዢዎቹ በበኩላቸው ለምን አገልግሎት እንነፈጋለን የሚል ጥያቄን ለአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ፅህፈት ቤት አቅርበዋል።

የከንቲባ ፅህፈት ቤቱ ባለፈው መስከረም ወር ውዝግቡ እልባት አስከሚያገኝ ድረስ ሌሎች አገልግሎቶች ይሰጡ የሚል ትዕዛዝን አስተላልፎ ነበር።

የየካ ክፍለ ከተማ መሬት ልማት ማኔጅመንትም ከከንቲባ ፅህፈት ቤቱ ለመጣው ደብዳቤ አገልግሎቱን መስጠት አልችልም የሚል ምላሽ ሰጥቷል።

የጊፍት ቢዝነስ ግሩፕ ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ ገብረኢየሱስ ደግሞ፥ ከመጠየቃችን በቀር የመከልከላችንን ምክንያት አናውቅም ብለዋል።

የፅህፈት ቤቱ ደብዳቤ ግን አገልግሎቱን ለመከልከሉ ሁለት ምክንያቶችን ይጠቅሳል፤ ጊፍት ሪል ስቴት መሪ ሎቄ እና አያት ባለው ሳይቱ ላይ ያለአግባብ የያዘው መሬት መኖሩና መሬቱ ለመንግስት እንዲመለስ ለማድረግ የተስተካከለ ካርታ አልቀበልም ማለቱ ቀዳሚው ነው።

ከዚህ ባለፈም የሶስት አመት የተጠራቀመ የመሬት ሊዝ ክፍያ እያለበት ገንዘቡን አለመክፈሉ ደግሞ ሁለተኛው ምክንያት መሆኑን ይጠቅሳል።

የክፍለ ከተማው መሬት ልማት ማኔጅመንት ለከንቲባ ፅህፈት ቤት ምላሽ በሰጠበት ደብዳቤው፥ ሪል ስቴቱ በርታ አካባቢ ለሚገኘው መሬት ከ2005 እስከ 2007 ዓ.ም ድረስ የሶስት አመት ከ4 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ የሊዝ ክፍያ አለመክፈሉን ገልጿል።

የጊፍት ቢዝነስ ግሩፕ ማኔጂንግ ዳይሬክተሩ፥ ከክፍለ ከተማው መሬት ልማት ማኔጅመንት ፅህፈት ቤት ማግኘት የሚገባቸውን አገልግሎት ማጣታቸው የሊዝ ክፍያውን ላለመክፈላቸው በዋና ምክንያትነት ጠቅሰውታል።

በሪል ስቴቱ እና በመስሪያ ቤቶቹ መካከል ያለው ውዝግብ አሁንም የቀጠለ ሲሆን፥ ቤት ገዢዎቹም በማያውቁት እና ባልተሳተፉበት ድርጊት መብት የሆነ አገልግሎትን ተነፍገዋል።

 

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy