በዓሉ በየዓመቱ ከነሓሴ 16 እሰከ ነሐሴ 18 በትግራይ ክልል በድምቀት ይከበራል።
የትገራይ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ከባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ጋር በመሆን በዓሉ የአለም ቅርስ ሆኖ እንዲመዘገብ እየሰራ መሆኑን አስታውቋል።
ከነገ ጀምሮ በሚከበረው በዓልም በመቀሌና ዓብዪ ዓዲ ከተሞች በድምቀት ለማክበር የተለያዩ ዝግጅቶች የተደረጉ መሆኑን ቢሮው አስታውቋል።
በዘንድሮው የአሸንዳ በዓል ላይ ለመካፈልም የተለያዩ እንግዶችና ቱሪሰቶች ወደ ክልሉ በመግባት ላይ መሆናቸውን የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ገልጿል።