Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ከውጭ የተመለሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ታጣቂዎች የመልሶ ማቋቋሚያ ፕሮጀክት ጽህፈት ቤት ተቋቋመ

0 433

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ከውጭ የተመለሱ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ታጣቂዎች የመልሶ ማቋቋሚያ ፕሮጀክት ጽህፈት ቤት ተቋቋመ።

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ልዩ ሀላፊ አቶ ፍፁም አረጋ በትዊተር ገፃቸው ላይ መንግስት በውጭ ከሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ስምምንት መድረሱን አስታውሰው፤ ስምምነቱም ነፍጥ አንግበው የነበሩ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ታጣቂዎች ትጥቅ የሚፈቱበትን፣ ከህረተሰቡ ጋር የሚቀላቀሉብትንና ዘላቂ ኑሮ የሚመሩበትን ሂደት ይጨምራል።

ይህንን በአግባቡ ለመፈጸም በጠቅላይ ሚንስትር ጽህፈት ቤት ውስጥ የመልሶ ማቋቋሚያ ፕሮጀክት ጽህፈት ቤት መቋቋሙንም አስታውቀዋል።

ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ በዛሬው ዕለት አቶ ተስፉዬ ይግዙን የፕሮጀክቱ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አድርገው መሾማቸውንም አቶ ፍፁም አስታውቀዋል።

የኢፌዴሪ መንግስት በውጭ ከሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ስምምንት መድረሱን ተከትሎ በውጭ ሀገራት የሚንቀሳቀሱ በርካታ የፖለቲካ ፓርቲዎች ወደ ሀገር ውስጥ ገብተው በሰላማዊ መንገድ ለመንቀሳቀስ መወሰናቸው ይታወሳል።

ከእነዚህም ውስጥ አርበኞች ግንቦት 7፣ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ)፣ የኦጋዴን ብሄራዊ ነፃ አውጪ ግንባር (ኦብነግ)፣ የአማራ ዴሞክራሲያዊ ሀይል ንቅናቄ እና ሌሎች የፖለቲካ ድርጅቶች ተጠቃሽ ናቸው።

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) እና የኦጋዴን ብሄራዊ ነፃ አውጪ ግንባር (ኦብነግ) በቅርቡ ልኡካቸውን ወደ አዲስ አበባ መላካቸው ይታወሳል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy