Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ህወሃትና ብአዴን ከወሰን ጋር ተያይዞ ያሉ ችግሮችን ተነጋግረው በአጭር ጊዜ ውስጥ እንደሚፈቱ አቶ አባይ ወልዱ ገለፁ

0 752

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ህወሃትና ብአዴን ከወሰን ጋር ተያይዞ ያሉ ችግሮችን ተነጋግረው በአጭር ጊዜ ውስጥ እንደሚፈቱ አቶ አባይ ወልዱ ገለፁ

ህወሃትና ብአዴን ከወሰን ጋር ተያይዞ ያሉ ችግሮችን ተነጋግረው በአጭር ጊዜ ውስጥ እንደሚፈቱ አቶ አባይ ወልዱ ገለፁ

 በአማራ እና ትግራይ ክልሎች መካከል ከወሰን ጋር ተያይዝው የሚስተዋሉ ችግሮችን ህወሃት እና ብአዴን በመነጋገር በጋራ በአጭር ጊዜ ውስጥ እንደሚፈቱት የትግራይ ክልል ርእሰ መስተዳደሩ ገለፁ።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳዳሩ እና የህወሃት ሊቀመንበር አቶ አባይ ወልዱ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ በሰጡት መግለጫ፥ የትግራይ እና አማራ ህዝቦች በደም የተሳሰሩ ጠንካራ ግንኙነት ያላቸው፤ ትናንት ደርግን ለመጣል እና ዛሬ ደግሞ ድህነትን ለማሸነፍ በጋራ የተዋጉ እና እየተዋጉ ያሉ ህዝቦች ናቸው ብለዋል።

በመሆኑ የራሳቸውን አጀንዳ ይዘው የሚንቀሳቀሱ ፀረ-ሰላም ሀይሎች ሁለቱን ህዝቦች ለመለያያት የያዙት አጀንዳ አይሳካም ብለዋል።

ክልሎቹ ከወሰን ጋር ያሉ ችግሮችን በአጭር ጊዜ ውስጥ ለመፍታት በጋራም ይሰራሉ ነው ያሉት።

ከወልቃይት የማንነት ጥያቄ ጋር በተያያዘ እስካሁን ለክልሉ መንግስት የቀረበ ጥያቄ እንደሌለ በማንሳት፥ ከቀረበ ግን የክልሉ መንግስት እንደሚያየው ርእሰ መስተዳድሩ አረጋግጠዋል።

FBC

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy