Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

በኢህአዴግ እንደገና መታደስ ዙሪያ በፌዴራል መስሪያ ቤቶች በሚገኙ የድርጅቱ የመካከለኛ አመራር አካላት የሁለት ቀናት ግምገማዊ ስልጠና መድረክ ተካሄደ

0 505

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

በኢህአዴግ እንደገና መታደስ ዙሪያ በፌዴራል መስሪያ ቤቶች በሚገኙ የድርጅቱ የመካከለኛ አመራር አካላት የሁለት ቀናት ግምገማዊ ስልጠና መድረክ ተካሄደ
14355062_1216451395044672_873691801843251660_n

በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የመስብሰቢያ አዳራሽ ከሁሉም የፌዴራል ተቋማት የተውጣጡ የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች የመካከለኛ አመራር አካላት የኢህአዴግ ምክር ቤት የሀገሪቱን ወቅታዊ ነባራዊ ሁኔታዎችንና ድርጅቱ አሁን ላይ ያለበትን ነባራዊ ሁኔታ በመገምገም የለያቸውን ስኬቶችንና ውስንነቶችን መሰረት በማድረግ የተላለፈውን እንደገና በጥልቀት የመታደስ ድርጅታዊ ውሳኔ የተመለከተ የሁለት ቀናት ውይይት አካሄደዋል፡፡

መስከረም 9 እና 10 2009 የተካሄደውን ይህን የመካከለኛ አመራር መድረክ የመሩት የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚና የትምህርት ሚኒስትር አቶ ሽፈራው ሽጉጤ በኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚና ምክር ቤት እንዲሁም በከፍተኛ አመራሩ እንደገና በጥልቀት የመታደስን ድርጅታዊ ተሃድሶ አስመልክቶ በተካሄዱ ድርጅታዊ መድረኮች በግምገማ እስካሁን ባለው የሀገራችን የህዳሴ ጉዙ የመጡ ስኬቶችንና ያልተቀረፉ ችግሮችና ተግዳሮቶች ዙሪያ የተለዩ ጉዳዮችንና የተላለፉ ውሳኔዎችን ለተሳታፊ አመራሮች አቅርበዋል፡፡ በተጨማሪም ተሃድሶው የሚከተላቸውን አቅጣጫዎችና የሚጠበቁ ግቦችን የተመለከተ ገለፃ ቀርቦ አመራሩ ለውይይት በቀረቡ በርካታ ጉዳዮች ዙሪያ አስተያየት በመስጠት፣ ጥያቄ በመጠየቅና በተጨማሪነት የሚነሱ ጉዳዮች ካሉም እንዲያነሳ ማድረግ ተችሏል፡፡

ለሁለት ቀናት በተካሄደው መድረክ በርካታ ቁጥር ያላቸው አመራሮች የነቃ ተሳትፎ በማድረግ ከላይ በተቀመጠው አግባብ በርካታ ጉዳዮችን በአስተያየት፣በተጨማሪነትና በጥያቄ ከሚሰሩበት፣ ከሚኖሩበትና ከትውልድ አካባቢያቸው ካለው ተጨባጭ ሁኔታ ጋር በማያያዝ በአመራሩ፣ በአባሉና በህብረተሰቡ የሚስተዋሉ ዝንባሌዎችንና ተግባራትን አንስተዋል፡፡ ኢህአዴግ በምክር ቤትና በከፍተኛ አመራር ደረጃ በገመገመው አግባብ ችግሮችን ውስጣዊ አድርጎ እንዲፈቱ በማድረግ በኩል ሰፊ ክፍተት እንደነበር መካከለኛ አመራሩ በተመሳሳይ የገመገመ ሲሆን በተለይ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሩ እንዲሁም አባሉና መላ ህብረተሰቡን በማሳተፍ በጋራ ተቀራርቦ ችግሮችን በጊዜና በአግባቡ እየለዩ መፍትሄ ያለመስጠት ችግር እንደነበር አስቀምጠዋል፡፡

በአጠቃላይ በእስካሁኑ የህዳሴ ጉዞ ሀገራችን እጅግ የሚያማልሉና የሚያስጎመዡ ስኬቶችና ድሎች ባለቤት መሆን የቻለች ቢሆንም በአፈፃፀም መጓደል የተፈጠሩ ችግሮች እንዲሁም እየመጣ ካለው ልማት ጋር ተያይዞ በርካታ አዳዲስ የህብረተሰቡ የልማት ፍላጎቶች የተፈጠሩበትና ለወጣቱ የስራ እድል በሚገባ መፍጠር አለመቻሉ ሰፊ ውይይት ተደርጎበት መግባባት ተደርሷል፡፡ ለዚህም በአመራሩ በኩል ስልጣንን ለህብረተሰቡ ተጠቃሚነት ከማዋል በተያያዘ ክፍተት የነበረ መሆኑ፣ የአርሶ አደሩ ምርታማነት ደረጃ ሰፊ መራራቅ ያለበት መሆኑ፣ በገጠር ለአርሶ አደሩ የሚቀርበው የፋይናንስ ስርዓት በተደራሽነትነትና በአሰራር ክፍተት ያለበት መሆኑና ሌሎችም ተጨማሪ ችግሮች በመኖራቸው ምክንያት በድምሩ በከተማም ይሁን በገጠር ሞጋች ህብረተሰብ ሊፈጠር አስችሏል፡፡

በመሆኑም ይህንኑ ሀገራዊና ድርጅታዊ ሁኔታ መሰረት በማድረግ የኢህአዴግ ምክር ቤት እንደገና በጥልቀት ድርጅታዊ ተሃድሶ ለማድረግ መወሰኑ አግባብነት ያለው ውሳኔ መሆኑን መካከለኛው አመራር ያረጋገጠ ሲሆን ለተግባራዊነቱም የበኩሉን እንደሚወጣ አረጋግጧል፡፡

በውይይቱ ማጠቃለያም የድርጅቱን ተሃድሶ በሚገባ ተግባራዊ ማድረግ አሁን በሀገራችን በየደረጃው የተለዩ ችግሮችን ከመፍታት አልፎ ለተጨማሪ ሀገራዊ ስኬቶች እውን መሆን ትልቅ አቅም የሚፈጥር ጭምር በመሆኑ በነቃ ተሳትፎ የአመራሩን፣ የአባሉንና የመላ ህዝቡን አቅም በማስተባበር ወደ ተግባር እንዲገባ ማድረግ አስፈላጊነት ተገልጿል፡፡

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy