Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

በወሰን ማካለል የተነሱ ችግሮችን ለመፍታት ክልሉ ቁርጠኛና ዝግጁ ነው—ርእሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው

0 639

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

በወሰን ማካለል የተነሱ ችግሮችን ለመፍታት ክልሉ ቁርጠኛና ዝግጁ ነው—ርእሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው

በአማራና በትግራይ ክልሎች በወሰን ማካለል ላይ የተነሱ ችግሮችን ለመፍታት ክልሉ ቁርጠኛና ዝግጁ መሆኑን ርዕሰ መስተዳድሩ አስታወቁ፡፡

በጎንደር ከተማ ከተለያዩ የህብተሰብ ክፍል ተወካዮች ጋር ወቅታዊ ጉዳዮችን አስመልክቶ በተደረገው ውይይት ህብረተሰቡ ለሰላም ያለውን ዝግጁነት ያሳየበትና ለችግሮቹም መፍትሄዎችን በማቅረብ በኩል መግባባት የተፈጠረበት ነበር ብለዋል፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ እንዳመለከቱት በሁለቱ ክልሎች መካከል የወሰን ጥያቄ ከተነሳ ረጅም ዓመታት ቢያስቆጥርም በተለያዩ ምክንያቶች እየተጓተተ ሳይፈታ መቆየቱን ገልጸልዋል።

ሳይፈታ በመቆየቱም ጭቅጭቅና ወደ ግጭት ሊያመሩ የሚችሉ ችግሮች እንዲፈጠሩ ማድረጉን ጠቁመው ችግሩን በፍጥነት ለመፍታት ሁለቱ ክልሎች የጋራ መግባባት ላይ መደረሳቸውን ገልጸዋል፡፡

ክልሉ ይህን ችግር ለመፍታት ቁርጠኛና ዝግጁ መሆኑን ያስታወቁት አቶ ገዱ ” እልባት በመስጠት ወደ ሌሎች አንገብጋቢ ወደሆኑ የክልሉን ዘላቂ ልማት በሚያፋጥኑ ጉዳዮች ላይ ማተኮር ያስፈልጋል “ብለዋል፡፡

ህብረተሰቡም በዚህ ረገድ ከክልሉ መንግስት ጋር በጋራ በመምከርና ገንቢ ሃሳቦችን በመስጠት ለችግሩ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እልባት ለመስጠት ተሳትፎውን ማጠናከር እንዳለበትም አሳስበዋል፡፡

“በጎንደር ከተማ ከተለያዩ የህብረተሰብ ተወካዮች ጋር የተካሄደው የጋራ ውይይት ህብረተሰቡ በግልጸኝነት ስሜቱን የገለጸበት መድረክ ነበር “ብለዋል፡፡

መድረኩ በችግሮች ላይ በዝርዝር መግባባት እንዲፈጠር ማድረጉንና ህብረተሰቡም የአካባቢውንም ሆነ የሀገሪቱን ተጨባጭ ሁኔታ እንዲገነዘብ ማገዙን ተናግረዋል፡፡

“ህብረተሰቡ የከተማውም ሆነ የክልሉ ሰላም እንዲጠበቅ ሃላፊነቱን ለመወጣት ቃል የገባበት መድረክ ነበር “ብለዋል፡፡

አመራሩ ህብረተሰቡ ችግሮች ያላቸውን ጉዳዮች ፈጥኖ ለማስተካከል ውሎ ሳያድር ወደ ተግባራዊ እንቅስቀቃሴ የገባበት ሁኔታ መኖሩንና ቀጣይ መድረኮችንም እስከ ታችኛው አካል ድረስ ለማውረድ ዝግጅት መደረጉን አቶ ገዱ አስታውቀዋል
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy