Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከላይ አርማጮሆ ወረዳ ነዋሪዎች ጋር ተወያዩ

0 1,342

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከላይ አርማጮሆ ወረዳ ነዋሪዎች ጋር ተወያዩ

አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከላይ አርማጮሆ ወረዳ ነዋሪዎች ጋር ተወያዩ

የአማራ ክልል ርዕስ መስተዳደር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የላይ አርማጮሆ ወረዳ ነዋሪዎችን የወልቃይት ጠገዴን የማንነት እና የድንበር ጉዳይን በተመለከተ አወያይተዋል።

ርዕሰ መስተዳደሩ በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት የጠገዴን እና ፀገዴን ድንበር ሁለቱ ክልሎች ተናጋግረው በአጭር ጊዜ ውስጥ መፍትሄ ይሰጣሉ ብለዋል።

የወልቃይት ማንነት ጥያቄም በትግራይ ክልል ቀርቦ ምላሽ ያገኛል ሲሉ ርዕሰ መስተደራደሩ ተናግረዋል።

በጐንደር የሚኖሩ የወልቃይት ነዋሪዎች ጥያቄቸውን በሰለማዊ ሁኔታ የማቅረብ መብት እንዳላቸው የገለጹት አቶ ገዱ፥ በተለይም የወልቃይት ነዋሪዎች ጥያቄያቸውን ለትግራይ ክልል አቅርበው ምላሽ ያገኛሉ ብለዋል።

የኮሎኔል ደመቀ ዘውዱም በአማራ ክልል በጐንደር ከተማ ጉዳዩ የሚታይ እንደሚሆን ርዕሰ መስተዳደሩ አረጋግጠዋል።

በምንም ሁኔታ ኮሎኔሉ ከጐንደር ከተማ እንደማይወጣ አቶ ገዱ ለነዋሪዎቹ ተናግረዋል።

የታሰሩትም በግልፅ ጉዳያቸው እንዲታይ እና ቤተሰቦቻቸው እንዲጠይቋቸው ይደረጋል ማለታቸውን የአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት ዘግቧል።

 

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy