Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ከኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ

1 744

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ከኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ

የኦህዴድ መእከላዊ ኮሚቴ ከመሥከረም 4-10/2009 ዓ.ም በአዳማ ባካሄደው ጥልቅ የተሀድሶ ግምገማ የድርጅቱን የ15 ዓመታት የስኬት ጉዞ እና ያጋጠሙ ተግዳሮቶች በመገምገም የወደፊት አቅጣጫዎችን አስቀምጧል፡፡

ባለፉትአስራ አምስት አመታት በኋላ ቀርነት እና በድህነት ላይ በተካሄደው ዘመቻ በክልሉ የገጠርና የከተማ አከባቢ ብሩህ ተስፋ እንዲለመልም ማድረግ ተችሏል ብሏል፡፡
መግለጫው በግብርናና በገጠር ልማት እስትራቴጂ ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ፣ የግብርና ኤክስቴሽን በማስፋፋትና የቴክኖሎጂ አጠቃቀም በማሻሻል፣ የህዝቡ ጠላት የሆነ ድህነትን በመቀነስ አርሶአደሩ ኑሮውን አንዲያሻሽል የተኬደው ርቀት አብይ ማሳያ መሆኑን ገልጾ ለዚህ ምስክሩ ተጠቃሚ መሆን የቻለው የኦሮሞ ህዝብ ነው ብሏል፡፡

ድርጅቱ በመግለጫው ለተገኘው ስኬት ለአርሶ እና አርብቶ አደሩ እንዲሁም የግብርና በለሙያዎችን አመስግኗል፡፡
የአርብቶአደሩን አከባቢ ልማት በተመለከተ የእርብቶ አደሩን ሕይዎት ለማሻሻል ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት አርብቶ አደሩ የመሠረት ልማት አውታሮች ፣ የትመህርት ፣ የጤና ፣ የመጠጥ ውኃ፣ የእንስሳት የገቢያ ትስስር ፣የእስሳቶች የጤናና የኤክስቴንሸን አገልግሎት እንዲያገኝ በተደረገው ጥረትም ተስፋ ሰጪ ውጤት ተመዝግቧልም ብሏል፡፡

ገጠሩን የኦሮሚያ ክልል ከኋላ ቀርነት ለማላቀቅ በሰው ሀብት ልማት ላይ በተሰራው ስራ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች ከቀዬያቸው ሳይርቁ የትህምርት ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ በተሰጡ ትኩረትም የተገኘው ውጤት አኩሪ ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡

ኦህዴድም ይህንን ድል ለማስመዝገብ ከባለእርሻ አካላት፣ ጋር በቅንጅት መስራት በማቻሉ ስለሆነ ለተገኘው ውጤት ላቅ ያለ ምስጋና አለው ብሏል፡፡

ገጠሩ የኦሮሚያ አከባቢ ከተለያዩ በሽታዎች አስቀድሞ ለመከላከል በተደረገው ጥረት ትልቅ ለውጥ ከማምጣት ባሻገር የምዕተ አመቱን የልማት ግቦች እንዲሳኩ አስተዋጽኦ አበርክቷል፡፡ በተለይ ለእናቶችና ህጻናት ጤና አጠባበቅ ፣ተላላፊ በሽታዎችን ለመቆጣጠር በተዘረጋው አሰራር የተሸለ ውጤት ማምጣት ተችሏል ብሏል መግለጫው፡፡

በሁሉም ረገድ የሚከናወኑ የልማት እንቅስቃሴዎች መሠረት እንዲኖራቸውና በመሠረት ልማት ዝርጋታ የመንገድ ፣ የመጠጥ ወኃ፣ የኤሌክትክ ኃይል አቅርቦት የቴሌኮም መስፋፋት በአንድ ክፈለ ዘመን ተሰርቶ በማይታወቅ መልኩ መስፋፋታቸውን ገልጾ የፕሮጀክቶች መጓተት በተደራሽነት እና ጥራት በኩል ውስንነቶች ያሉ ቢሆንም የተከናወነው ተግባር በየትኛው መስፈርት የሀገርቱን የመሠረተ ልማት ዝርጋታ ታሪክ የቀየረ መሆኑን አመልክቷል፡፡

የከተማና የገጠሩ ነዋሪዎችን በማስተሳሰር፣ ዘላቂ ልማት እንዲኖር ፣ ከተማን ለኑሮ ምቹ ለማድረግ እና የእንዱስትሪ መዕከል እንዲሆን ውጤታማ የሆኑ ትላለቅ ስራዎች ተስርቷል፡፡ በተለይ በከተማ በስፋት የሚስተዋለውን ስራ አጥነትና ድህነትን በመናድ የስራ በህል እንዲጎለብት ተደርጋል ብሏል መግለጫው፡፡

በገዢ መደቦች ተገፍቶና ተቀብሮ የነበረው የኦሮሞ ህዝብ ታሪክና ባህል ኦህዴድ በከፈለው አኩሪ መስዋእትናነት ባለፉት 15 ዓመታት የኦሮሞ ህዝብ አንገት ቀና ያስባለ ድል ማጎናጻፍ መቻሉን ገልጿል፡፡

በዚህም አፋን ኦሮሞ የመንግስት የሥራ ቋንቋ፣ የጥናትና ምርምር፣ የሣይንስና ቴክኖሎጂ እንዲሁም የመገናኛ ብዙሀን ቋንቋ ማድረግ መቻል ትልቁ ማሳያ ነው፡፡የኦሮሞ ህዝብ ታሪክ ተደብቆ ከነበረበት ይፋ እንዲወጣ በአፈ ታሪክ ሳይሆን በፅሑፍ ለትውልድ እንዲተላለፍ ማድረግ ተችሏል፡፡ምቹ መደላደልም ተፈጥሯል ብሏል፡፡
ከዚህ ባሻገር ከኦሮሞ ህዝብ ጋር ቁርኝትና ልዩ ትርጉም ያለቸውን ታሪካዊ ስፍራዎችን ልዩ ትኩረት በመስጠትና በማልማት ድርጅቱ ከትውልድ ትውልድ የሚተላለፍ ታሪካዊ ሃውልት ማቆም ችሏል፡፡
በዚህ አጋጣሚ ለታሪኩ ቀጣይነት የኦሮሞ አገር ሽማግሌዎች ሙሁራንና የድሉ ባለቤት የሆነው አዲሱ ትውልድ ትልቅ ደስታና ስኬት ነው ብሎ ያማናል ብሏል መግለጫው፡፡

ኦህዴድ ካስመዘገባቸው ታሪኮች ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የክልሉ ሚዲያ በማቋቋም የኦሮሞን አንድነት፣ ታሪክና ቋንቋን በማሳደግ ህዝቡ ወቅታዊ መረጃ እንዲያገኝ ከመላው ሀገሪቱ ጋር እንዲገናኝና ከአለም ጋር እንዲተሳሰር፣ ህዝቡን ለማህበራዊና ለልማት ስራዎች ተነሳሽነት እንዲኖረው፣ የልምድ ልውውጥ እንዲያደርግ ልማታዊ ተልዕኮ ያለውን ሚዲያ መስርቶ መስራት መቻል ትልቅ ስኬት መሆኑም ሊታወቅ ይገባል፡፡
አህዴድ የስራውን ስኬት ሁሌም ሲገመግም ያለፈውን የስራ መነሻና ባስመዘገበው ውጤት ተኩራርቶ እራሱን ለመመፃደቅ ሳይሆን ውጤቶቹ ያላቸው ትርጉም እና ሚስጥር ለወደፊት ትግሉ ያላቸውን አስታዋጽኦ ከግምት በማስገባት የገጠሙ ወስንነቶችን ትምህርት በመውሰድ ለቀጣይ መዕራፍ እራሱን ለማዘጋጅት ነው።

ከሁሉም በላይ ደግሞ የልማትና የዲሞክራሲ አቅጣጫውን የራሱ አድርጎ የድርጅቱን ባህሪ በመረዳት በጥንካሬም ሆን በድክመታችን ጊዜ በመገሰፅና በመምከር አሳድጎና ስልጣኑን በመስጠት መቼም ቢሆን ጥቅሙ እንዲከበርለት በድርጅቱ ላይ እምነቱን በመጣልና ተስፋ በማድረግ ኃላፊነቱን ለሰጠው ህዝብ ድርጅቱ ሙሉ እመነት አለው፡፡ላለፉት 15 ዓመታት ባካሄድነው ትግል ያጋጠሙን ችግሮች በስራ ሂደት ያገጠሙ ችግሮች እንጂ የአቅጣጫ ችግር ያለመሆኑ ሊሰመርበት ይገባል፡፡

ከዚህ ችግር በመማርና በማስተካከል የህዳሴውን ምዕራፍ መሠረት ለማስያዝ ስምምነት ላይ ደርሰናል፡፡ዋነኛው ችግሮች ናቸው ብለን ከለየናቸው መካከል የህዝባዊ ወገንተኝነት ላይ ያለ አመለካከትና አብዮታዊ ዲሞክራሲ መሠረት በማድረግ በየደረጃ እያደገ የመጣው ከራስ ወዳድነት የተነሳ ስልጣን የህዝብን ማገልገያ መሣሪያ መሆኑን በመዘንጋት ከህዝብ በፊት እራስን መለወጥ የህዝብ አገልግሎት እየተጓደለ በመምጣቱ በአስቸኳይ እነዚህን ችግሮች በማስተካከል ወደ ህዝባችን ልንመለስ ይገባል በሚል አቋም የትግላችንን ቃል እናድሳለን፡፡

ከዚህ ቀደም የነበረንን ህዝባዊ ወገንተኝትነት ስናጓድል ቅሬታና ኩርፊያ እንዳለው በተለየ ሁኔታ ስላሳየ የህዝቡን ቅሬታ ለመቅረፍ ለመልካም አስተዳደርና የልማት ጥያቄዎችን በነቃ የህዝቡ ተሳትፎ እንደምንመልሰው ማረጋገጥ ተገቢ ነው፡፡በሌላ በኩል የመልካም አስተዳደር ችግሮችና በገጠርና በከተማ ያለው የስራ አጥነት ችግር ለመቅረፍ በሁሉት አቅጣጫ ተመልክተናል የመጀመሪያ እየጨመረ የመጣው የህዝቡ የመለወጥና የመልማት ፍላጎት ካጋጠመን የማስፈጸም አቅም ወስንነት በሚፈለገው መጠን ሟሟላት አልተቻለም ፡፡ በዚህም ህዝቡ ቅሬታ ቢኖረውም የጊዜ ጉዳይ ካልሆነ በቀር በኛ ትግልና የህዝቡ ታሳትፎ ችግሮችን እንደምንቀርፍ በመገንዘብ ህዝቡ በትዕግስት እንዲጠብቀን በከፍተኛ አክብሮት እንጠይቃለን፡፡

በዉስጥ አፈፃፀም ችግሮች ለጋጠመው የመልካም አስተዳደር እጦት ሕዝባችንን በክብር ይቅርታ ጠይቀን በከፍተኛ የዉስጥ ትግል እና የሕዝቡ ድጋፍ ሠርተን ሕዝቡን ለመካስ ቃል እንገባለን፡፡
በዉስጥ ችግራችንና እንከኖቻችን የተነሳ የገጠሙ ችግሮችን በመጠቀም በክልሉ ፀረ-ሰላም ሀይሎች ባናፈሱት አሉባልታ የፀጥታ ችግር ምክኒያት ለጠፋዉ የሰዉ ሕይወት እና ንብረት ዉዱመት የተሰማንን ጥልቅ ሃዘን እየገለፅን የጥፋት ሃይሎች ስረዓቱን ከመሠረቱ ለመናድና ድሎቻችንን ወደ ኋላ ለመመለስ ያደረጉት መፍጨርጨር ባለበት ቦታ እንዲቆምና ችግሮቻችንን እንደ ተለመደዉ በዉይይት መፍታት እንዳለብን ለህዝባችን ጥሪ እናቀርባለን::

የጥፋት ሀይሎች አገርንና ስራዕቱን ለመናድ ያላቸዉን ተልዕኮ እንደተለመደዉ ትግሉ የሚጠይቀዉ መስዋዕትነት በመክፈል የምንታገል ሲሆን ለዚሁ የተለመደዉን የኦሮሞ ሕዝብ ድገፍ እንጠይቃለን ፡፡
የፀረ-ሰላም ሃይሎችም በአቋራጭ በብጥብጥ ስልጣን ለመያዝ የሚያደርጉት እንቅስቃሴ መቼም ሊሳካ እንደማይችል ተረድተዉ ከአሸባሪነትና ብጥብጥ ስራቸዉ እንደታቀቡ በድጋሚ ማሣሠብ እንወዳለን ፡፡
1ኛ ድርጅታችን ከየትኛዉም ዉጫዊ ችግር በማስቀደም በመጀመሪያ ዉስጣዊ ችግሮቹን በጥልቀት በመመርመርና በማጥራት ድርጅታችንን በማጠናከርና ወደ ሕዝባዊ ወገንተኝነት በመመለስ ትግሉን በማቀጣጠለል ለሮሞ ሕብብ ጥቅምና መብት ልክ እደትላንቱ በቆራጥነት ለመተገል ዝግጁ መሆናችችንን እናረጋግጣለን፡፡

2ኛ ድርጅታን ኦህዴድ ስልጣን የህብረተሰባችንን ሁንተናዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጫ መሳሪያ መሆኑን ከመገንዘቡ የተነሳ የህዳሴያችንን ጉዜ ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር እንዲያስችልን ለህዘቡ ያለውን ወገንተኝነት እራስ ላይ አስከመወሰን ድረስ ለመግለፅ የድርጅታችን ከፍተኛ አመራሮች ከኃላፊነታቸው በራሳቸው ፍቃድ ለመውረድ ለማዕከላዊ ኮሚቴው ጥቃያቄ በማቅረብ የድርጅቱ ሊቀመንበርና ምክትል ለቀመንበር ያቀረቡትን ጥያቄ ማዕከላዊ ኮሜቴው ውሳኔያቸውን በታላቅ አፅንዖት አይቶ በመወሰንና በአመራርነታቸው የነበራቸውን ተሳትፎ ግምት ውስጥ በማስገባት አንድ እርከን ዝቅ በማድረግ የድርጅቱ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ሆነው እንዲቀጥሉ ወስኗል፡፡

በምትካቸውም አዲስ የድርጅቱ ሊቀመንበርና ምክትል ሊቀመንበር ተተክቷል፡፡
3ኛ በተጨማሪ በአመራርነታችን ክፍተት የመጡ ችግሮችን በጥልቀት በመመርመር የድርጅቱንና የመንግስትን ጠንካራ መዋቅር በማረጋገጥ የትግሉ ምዕራፍ የሚጠይቀውን አመራርነት ለመስጠት የህብረተሰባችንን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ዝግጁነታችንን እንገልጻለን፡፡

4ኛ የህበረተሳባችንን የእለት ተእለት ኑሮ ጠፍንጎ የያዙ የመለካም አስተዳደር ችግሮችን በመለየት የችግሮቹን ምንነት በየደረጃው ለመፍታት ህበረተሰቡን ባሰተፈ መልኩ ትኩረት ሰጥተን የምንሰራ ይሆናል፡፡የኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከትና ድርጊትን ያለምንም ምህረት ድል በማድረግ ለህዳሴያችን ጉዞ ስኬት እልህ አስጨራሽ ትግል እናደርጋልን፡፡ለዚህም የእናንተን የተለመደውን ርብርብ እንሻለን፡፡

5ኛ የህዳሴያችንን ጉዞ በአንድ ሌሊት ከዳር ማድረስ አዳጋች መሆኑ እውን ነው፡፡የህዳሴው ጉዞ በሂደትና ቀጣይነት ባለው መልኩ ከተሰበበት የሚደርስ መሆኑ ይታመናል፡፡በመሆኑም በጥልቀት ለመታደስ በአመራሩ ፣በሰፊው አባላትና በህዝቡ ዘንድ ደርሶ መሠረታዊ ለውጥ ለማምጣት ያላንዳች እርፍት እንደምንሳራና ለህዳሴያን ስኬት የሁላችን ድርሻ ከፍተኛ በመሆኑ ዛሬም እንደትናንቱ በእኔነት ስሜት እንድትረባረቡ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

6ኛ -አንድነታችን በማጠናከር ተጠቃሚነታችንን እንደምናረጋግጠው ሁሉ ከአገራችንና ጎረቤቶች ሕዝቦች ጋር በወንድማማችና መቻቻል ቅርርብ በመከባበር ልክ እንደ ትናንቱ ዛሬም ክንዳችንን አጠናክረን በድሕነትና ኋላ ቀርነት ላይ የጀመርነዉን ትግል አጠናክረን በማስቀጠል ለአገርቱ የሕዳሴ ጉዞ ስኬት የበኩላችንን ድርሻ እንወጣለን፡፡

7ኛ፡- የሕዝቡንና የዴሞክራሲ ተቋማትን ግንባታና አደራጃጀት በማጠንከር በሁሉም ዘርፍ የሕዝቡን ተሣትፎ በተደራጁ መልኩ በማረጋገጥ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታውን መሬት በማስያዝ እያሣደግን ለመሔድ የሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ በትኩረት ለመስራ ዝግጁ መሆናችንን እናረጋግጣለን፡፡

8ኛ አገራችን በደረሰችበትን አገራዊ እድገት መሠረት የሕዝብ ልማት ስራችን በከፍተኛ ሁኔታ እያደረገ መቷል፡፡ይሁን እንጅ በክላችን የተማረው ኃይልና ወጣቱ በሚፈለገው መልኩ ተጠቃሚ መሆን ባለመቻሉ ወጣቱና ቤተሠቦቻቸው ትክክለኛ ጥያቄ በመጠየቃቸው ድርጅታችን በከፍተኛ የተጠያቅነት መንፈስ እና ሙሉ እምነት በመቀበል ችግሩን ለመቅረፍ መስራት እንደጀመርነው በትኩረት በስፋት እንደምንሰራበት እና መሰረታዊ ለውጥ መምጣት እንደምንችል በሙሉ እምነት እንገልጿለን፡፡በዚሁ የክልላችን ወጣቶች የሚጠበቅባቸውን ድጋፍ እንዲያደርጉ እንጠይቃለን፡፡

9ኛ፡- ድርጅታችን ከሕዝባዊ ወገንተኝነቱ የተነሳ አርሶአደሩ በተደጋጋሚ የሚያነሳቸው ጥያቄዎች በተለይም በልማት ምክንያት ከመሬታቸው እንዲነሱ የተደረጉ አርሶአደሮችን ጉዳይ በጥልቀት በመመርመር ተጠቃሚነታቸውን በከፍተኛ ሁኔታ ለማረጋገጥ በጠንካራ አደረጃጀትና አሰራ በመደገፍ ከዚህ ቀደም በአፈፃተም ይታዩ የነበሩ ችግሮችን ከመሰረቱ በማጥፋት ተጠቃሚነታቸውን እናረጋግጣለን፡፡

10ኛ፡- በድንበር አካባ በተለያዩ ጊዜያት የሚያጋጥመውን ግጭት በልዩ ትኩረትና ቆራጥነት ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካት ጋ በመሆን ለመፍታ የምንሰራ መሆኑን በመግለፅ ሕብረተሰባችን ችግሮች ሲያጋጥሙ በሰላማዊና በተረጋጋ መንገድ ለማፍታት ርብርብ ማድረግ እንዳለበት ጥሪያችን እናቀርባለን፡፡

11ኛ፡- ሰላ ለሁሉም መሰረት መሆኑን ከሕብረተሰባችን በላይ የሚያውቅ አለ ብሎ መውሰድ አይቻል፣ም፡፡ ከምንም በላይ ያሉብብበ ችግሮች ትኩረት ሰጥቶ በማየት ለችግሩ እልባት ለመስጠት ብሎም ተጠቃሚ ለመሆን ወሳኙ ጉዳይ ሰላ ነው፡፡

ድርጅታችን ኦህዴድ ሁሌም ትልቁ ጠላታችን ድህነት ነው ብሎ ያምናል፡፡ ከዚህ በዘለለ በሰላማችንና ልማታችን ላይ እንቅፋት የሚሆኑት የጥፋት ኃይሎች ናቸው፡፡ ከዚህም ሌላ ሕገ-መንግስታዊ ስርዓቱን በኃይል በመናድ ስልጣንን በአቋራ ለመያዝ ለሚፈልጉ ኃይሎች ሕብረተሰባችን እንደማይፈቅድላቸው በተጨባጭ አረጋግጧል፡፡ስለዚህ ሕብረተሰባችን በሁሉም ደረጃ ትልቅ መስዋዕትነት በመክፈል በግንባር ቀደምትነት የአካባቢውን ሰላ ለማስከበር ላደረገው ርብርብ ታላቅ ክብር እናቀርብላቸዋለን፡፡
ከዚህም በኋላ ለኑሯችን መሰረት የሆነው ሰላም እንዳይደፈርስ ሕብተሰባችን አሁን ያደረገውን ትልቅ ተሳትፎ ተጠናክሮ በመቀጠል የጀመርነው ልማታችን ከዳ እንዲደርስ ከሕብረተሰባችን ጋር እጅ ለእጅ ተያይዘን ለመስራ ያለንን ዝግጁነት በግለፅ አሁንም ለሕብረተሰባችን ዳግም ጥሪያን እናስተላልፋለን፡፡
12ኛ፡- የአካባቢያችንን ሰላም ማረጋገጥ ወሳኝ እንደሆነ ሁ የሕግ የበላይነት መስፈንም ለዜጎቻን ኑሮ ትልቁ ዋስትና ነው፡፡ በመሆኑ ለዚሁ ስራ ስኬት የሰፊው ሕብረተሰባችን፤የፍትህ አካትና የፀጥታ አካት ድርሻ ወሳኝ ነው፡፡ እጅ ለእጅ ተያይዘን የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ ሁሉም ዜጋ ያንዳች ሥጋት የተጀመሩ የልማት፤የዴሞክራሲ ስርዓተር ግንባታ ስራዎችን ከለዳር ማድረስ እንዳለበት ጥሪያችንን እንቀርባለን፡፡

በመጨረሻ |የሕዳሴ ጉዞአችን እንዲሳካ በማድጉ ረገድ ከምንም በላይ መዋቅሮቻን በትልቅ ዝግጁነት እንዲተገብሩና እንዲያስተገብሩ እንዱሁም ሕብረተሰቡ እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ ተሳትፎውን ማጠናከር እንዳለበት ጥሪ እናቀርባለን፡፡

የሕዳሴያችን ጉዞ እንዲሳካና የሕብረተሰባችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት እውን እንዲሆን ርብርብ ማድረግ እንዳለባችሁ ታላቅ ጥሪ እናቀርባለን፡፡
የኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ
መስከረም 11/2009
አዳማ

  1. Mulugeta Andargie says

    Guys!!! You are always strong!!! We are beside you!!! Go for it!!!

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy