Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ወንጌላዊ ያሬድ ፣ አፈርኩብህ።

0 678

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ወንጌላዊ ያሬድ ፣

አፈርኩብህ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከአንተ የተሻሉ እንጂ ያነሱ አማኝ እንዳልሆኑ ልብህ ያውቀዋል። መሳሪያ የታጠቁ እና የዜጎችን ህይወት (የጸጥታ አስከባሪዎችን ጭምር) እየቀጠፉ ፣ ቤታቸዉን እና ንብረታቸውን እያጋዩ ያሉ ወንጀለኞችን እንደ ሰላማዊ ሰልፈኛ በመቁጠር ፣ ብዙ አልክ። የህዝብ እና የአምላክ ባለአደራ የሆኑትን መሪ ፣ ሃላፊነታቸውን እንዳይወጡ ለመማጸን ያደረግከው ሙከራም እጅግ አሳዝኖኛል። በሃገራችን የተወሰኑ አካባቢዎች በተፈጠሩት አሳዛኝ ሁኔታዎች የተጎዳው ፣ በጎዳናው ነውጥ ላይ ካየሃቸው የተወሰኑ ሰዎች በላይ ብዛት ያላቸው ፣ ሰላማዊ ወገኖች እና ሃገር ናቸው። ምንም እንኳን የተመቸ ዘመን አማኝ/ሰባኪ ብትሆን ፣ በቀደመው ስርአት አማኝ መሆን እጅግ የከፋ ዋጋ የሚያስከፍል ወንጀል እንደነበር ሳትሰማ ወይም በሩቅ ሳታይ ኣትቀርም። አንተን በእኩልነት እና በነጻነት እንድታመልክ እና ያማረ ኑሮ ማግኛ መንገድ እንዲከፈትልህ ያደረገ ይህ ስርአት ፣ ዛሬም በተለያየ መንገድ በጭንቅ ውስጥ ላሉ እና ድረሱልን ለሚሉ ዜጎች የመድረስ እና ከወንበዴዎች ስራ የመታደግ ሃላፊነት እና ግዴታ ኣለበት። በዚህ ፈታኝ በሆነ ሰአት የሃገርን ሰላም እና መረጋጋት እንዲያስከብር ሰራዊቱን ማዘዝ የትጋ ነው ችግሩ? አንተ የእዛ አካባቢ ነዋሪ ብትሆን መንግስት ዝም ብሎ እንዲያይህ ትፈልግ ነበር?
በርካታ የእምነት ሰዎች ደግመው ፣ ደግመው እንደ ተናገሩት ይህ ዘመን አምላክ በቃሉ መሰረት ምድራችንን ያሰበበት የከፍታ ዘመን ነው። ትናንት ከብዙ ፈተናዎች በድል እንድንወጣ ያስቻለን አምላክ ከዚህም ጊዜያዊ ችግር እንድንወጣ ሊረዳን የታመነ ነው። በምድሪቱ ላይ የሆነው ተአምራዊ ለውጥ ሁሉ በሰው ብቻ የተከናወነ አለመሆኑን እስካሁን ካልተረዳህ መንፈስህ ከየት እንደሆነ ያጠራጥረኛል።
በመጨረሻም ፣ አምላክ በእርግጥ መኖሩን እና በስራው ጣልቃ የሚገቡትን ሲገስጽ ፣ ደግሜ ደግሜ ማየቴን ልገልጽልህ እወዳለሁ።
ልክህን የምታውቅበት አና የማስተዋል ጸጋውን ያብዛልህ። ወደ ነፈሰበት ከመሄድ እና በሚያልፍ ፈተና የማያልፍ ትዝብት ውስጥ ከመውደቅም ይጠብቅህ።

Begashaw Kebede

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy