Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ተገቢ ትኩረት ያጣ አንገብጋቢ ጉዳይ

0 616

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ተገቢ ትኩረት ያጣ አንገብጋቢ ጉዳይ

በኢህአዴግ ድርጅታዊ መግለጫም ይሁን ጠቅላይ ሚንስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙርያ ለጋዜጠኞች በሰጡት ማብራርያ ላይ ቦታ ያልተሰጠው ነገር ግን በሀገራችን የተወሰኑ አካባቢዎች ለተፈጠሩ አሳዛኝ ሁኔታ ወሳኝ ሚና ያለው ጉዳይ አለ፣ ይኸውም የተከፈተብን የማህበረሰብ ዜና ማሰራጫዎች እና አጠቃላይ የ CYBER ጦርነት ነው። በተለያየ አቅጣጫ የሚመጡና በታሪካዊ ጠላቶቻችን በጥሩ ሁኔታ የሚደግፉ የጥፋት ሀይሎች ያሰማሯቸው እነዚህ የዜና ማሰራጫዎች እንኳን የሒወት ተሞክሮ ያነሰውን ወጣት እድሜ የጠገበውንም የማሳት አቅም አላቸው። ይህ ችግር በእኛ ሀገር ብቻ የተወሰነ ሳይሆን አለምን በአጠቃላይ እየፈተነ ያለ የዘመናችን ትልቅ ችግር ነው።በምእራቡ አለም የሚኖሩ የተወሰኑ ወጣቶችን ከሞቀ ኑሮአቸው አንስቶ መያዣ መጨበጫው ወደ ጠፋባቸው የእልቂት ቀጠናዎች እየወሰደ ያለውም ይኸው ሰይጣናዊ መንገድ ነው።የዋሆቹን የምእራባውያን ወጣቶች በሚኖሩባቸው ሀገራት ላይም እልቂትና ሰቆቃን ለማድረስ የአጥፍቶ ጠፊነት ተግባር እንዲፈጽሙ ማድረግ ተችሏል። የጥፋት እና የውድመት አጀንዳ ያላቸው እና ዋና መቀመጫቸውን በውጭ ሀገራት ያደረጉ አንድ አንድ የሀገራችን ድርጅቶች እና ግለሰቦችም ከእነ ISIS ገጽ በመዋስ ወጣቱ ላይ ያተኮረ የጥላቻ እና የአመጽ ቅስቀሳዎችን አካሂደዋል። ከአመታት በፊት በተለያዩ ሀገራት ላይ የደረሱ የሞት አደጋዎች ልክ በእኛ ምድር ላይ እንደተፈጸሙ በማስመሰል ያሰራጭዋቸው የቅስቀሳ መልእክቶች ብዙዎችን አሳዝኗል፣አስቆጥቷልም።ለዚህ ትልቅ ምሳሌ የሚሆነው የአትሌት ፈይሳ ሌሊሳ ታሪክ ነው።አትሌቱ እንደዚህ አይነት ትልቅ ውሳኔ ለመወሰን ያበቃው የቅርብ ጉዳይ ማለትም ከቤተሰቡ መሀል የታሰረ ወይም የተገደለ ሰው መኖር አለበት በሚል ግምት ጋዜጠኞች ጥያቄውን ሲያቀርቡለት የታሰረም የተገደለም ዘመድ እንደሌለው እና በሩቅ ሆኖ በሰማው ብቻ በማዘን ይህንን ውሳኔ ለመወሰን መቻሉን ነበር የገለጸው ።ባለቤቱም ምን እንደተሰማት እና እንደዚህ እንደሚያደርግ ጠብቃ እንደሆነ ከሮይተርስ ለቀረበላት ጥያቄ ስትመልስ ” በኢንተርኔት ዜናዎች ላይ እያየ በጣም ይበሳጭ ስለነበረ ይህንን ማድረጉ ብዙም አላስገረመኝም።” ነበረ መልሷ ሰሙኑንም ነዋሪነታቸው በቶሮንቶ ካናዳ የሆኑ የቅድስት ማርያም ቤተክርስትያን አስተዳዳሪ በአንድ ቃለ ምልልስ ላይ ከጠቀሱት እጅግ ካዘኑባቸው ጉዳዮች መካከል ቦርሳ ይዛ መንገድ ላይ ሬሳዋ የወደቀችን ሴትጉዳይ ነበር፡ያቺ ሴት ከአመታት በፊት በአንድ የአፍሪካ ሀገር የሆነ ታሪክ እና በጊዜው ዜና ማሰራጫዎች ካወጡት ዜና ላይ የተወሰደ መሆኑን በማስረጃ ተገልጿል።ይህን የገጠመንን ችግር እድገታችን ያመጣብን ችግር በማለት የሚገለጽበት ሁኔታ ትልቅ እውነትነት አለው። ዛሬ በገጠሪቷ ኢትዮጵያ ውስጥ ቀላል የማይባል ቁጥር ያላቸው ወጣቶች የማህበራዊ ዜና ማሰራጫዎች ተጠቃሚ ናቸው።ማለትም አገልግሎቱን ለመጠቀም የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶችን ( ሞባይል ስልኮች እና የመሳሰሉትን) የመግዛት አቅም ተፈጥሯል ማለት ነው። ሰልፎቹ ወይም ሁከትና ግርግሮቹ የሚጠሩትም በማህበራዊ ዜና ማሰራጫዎች ነው ። ባለቤት የሌላቸው ሰልፎች/ እንቅስቃሴዎች የሚባሉትም ለዚህ ነው። ታዲያ በግልፅ የሚታይ ይህ ሁኔታ እያለታዲያ በግልፅ የሚታይ ይህ ሁኔታ እያለ

ኢህአዴግ የወሰደው የችግሮቹ ምክንያት እኔ ነኝ በእኔ በኩል ያሉት ጉድለቶች በዝተው ነዉ ሕዝብ የተማረረዉ የሚል አቋም ከየት መጣ? አዎ ኢህአዴግ ራሱን መፈተሹ እና ማረሙ በጣም አስፈላጊና ድርጅቱ እስካለ ድረስ መቀጠል ያለበት ጤነኛ ሂደት ነዉ።ህዝቡም ከድርጅቱ የሚጠብቀው ይህንኑ ሲሆን ነገር ግን ሽብር እና ሁከት በሌለበት መንገድ የተወሰኑ አካባቢዎች አነስተኛ በሆኑ አካባቢዎች እና እጅግ አነስተኛ (በአብዛኛው ወጣቶች) የህብረተሰቡ ክፍሎች የተካሄደን የሽብር ስራ እንደ ህዝብ ተቃውሞ ከወሰድነው የአሸባሪዎች ህልም እውነት ሆነ ማለት ነው። በዚህ ሰአት ተግተው እየሰሩ ያሉት “የኢትዮጵያ ህዝብ ተነስቷል” የሚል እውቅና ለማስገኘት ነው። ሌላው ቀርቶ አብዛኛው የኦሮሞ እና የአማራ ወጣት እንኳን ያልተሳተፈበት ረብሻ እና ግርግር ነው እየታየ ያለው። ሀገራችን ኢትዮጵያ ላለፉት በርካታ አመታት የእድገት፣የሰላም እና የመረጋጋት ምሳሌ በመሆን ከፍ ብላ መታየት የጀመረችበት አኩሪ ሂደት ላይ ይህ ጥቁር ነጥብ የጣለ አጋጣሚ በአጭሩ መፈታት የሚችለው የችግሩን ምንጭ በትክክል መለየት ሲቻል እና መፍትሔ ሲያገኝ ብቻ ነው። ሽብርተኞቹ የያዙት አጀንዳ እና መፈክሮቻቸው ኢህአዴግ አለበት ከሚባለው አንዳንድ ድክመቶች ጋር ምንም ግኑኝነት የላቸውም። ኢህአዴግ በሆነ ተአምር ጉድለቶቹን መቶ በመቶ ማረም ቢችል እንኳን በሰልፍ ወይም በግርግሮች ላይ ለሚታዩ እና ለሚሰሙት ህገወጥ ባንዲራዎች እና መፈክሮች መልስ ሊሆኑ አይችሉም እነዚህን በማህበራዊ ዜና ማሰራጫዎች የሚንቀሳቀሱ የህብረተሰብ ክፍሎች እንደ ሁልግዜው ብዙሀኑን የህብረተሰብ ክፍል ከጎኑ በማሰለፍ የሚመለሱትን ለመመለስ በመሞከር እና ችግሩን ፊት ለፊት በመጋፈጥ ሊወጣው ይገባል። ደስ የሚለው ሌላው ጉዳይ ግን አብዛኛው የህብረተሰብ ክፍል ” ከምሰማው ይልቅ የማየውን ነው የማምነው ” የሚል አቋም አቋም ያለው መሆኑ ነው።ለዚህም ትልቅ ምሳሌ መሆን የሚገባው የአዲስ አበባ ወጣት እና አጠቃላይ ነዋሪ ነው።የማህበራዊ ዜና ማሰራጫዎች ተጠቃሚነቱ ከሌሎች አካባቢዎች ከፍ ያለ ሆኖ ሳለ ከአመታት በፊት ያደርግ እንደነበረው ከተማይቱን ወጥቶ እንዲያጥለቀልቅ ለቀረበለት ጥያቄ የሰጠው ምላሽ “ጆሮ ዳባ ልበስ” ነበር።ለዚህም ዋናው ምክንያት ባለ ራእይ መሪዎቻችን እና ህዝቡ በመተባበር የሚልዮኖች ማደርያ የሆነችው መዲና ላይ ላለፉት በርካታ አመታት የሰሩት አኩሪ ስራ እና ህብረተሰቡ ካለፈ ስህተት ያገኘው ትምህርት ነው ማለት ይቻላል።እነ ባህርዳር እና ጎንደርም ዛሬ ከሚያልፉበት የማይመች ሁኔታ ትምህርት እንደሚያገኙበት እና ዳግም እንዳይከሰት ማድረግ እንደሚቻልም አምናለሁ።

እነዚህ አካባቢዎችም ቢሆን ለደረሰው ችግር በተቀናጀ መልክ የሚንቀሳቀሱ እና ሁከት እና ብጥብጡን በአጠቃላይ ፀረ ህዝብና ፀረ ሀገር ድርጊቶችን የሚመሩ ጥቂት ኃይላት እና እጅግ አነስተኛ የሆነ የህብረተሰብ ክፍል እንጂ ተጠያቂው በመቶ ሺዎች እና በሚሊዮኖች የሚቆጠረው የአካባቢዎቹ ነዋሪዎች እጃቸው ከደሙ ንፁህ ነው። በአንድ አነስተኛ ከተማ ውስጥ በዳሽን ቢራ ፋብሪካ ንብረት ላይ የተፈጸመው የውንብድና ስራም በህብረተሰቡ እና በጣም አነስተኛ በሆኑት በሽብር ስራ ላይ የተሰማሩት ግለሰቦች መሀል ያለውን ልዩነት በግልጽ ማሳየት የሚችል አጋጣሚ ነበር። 20 ግፋ ቢል 30 የሚሆኑ ጎረምሶች የውድመቱ ስራ ሲሰሩ እና በተከመረው የቢራ ሳጥን ዙርያ እየተሽከረከሩ ሲያብዱ በርካታ የአካባቢው ነዋሪዎች አይናቸውን ለማመን በመቸገር እና በመገረምፈዘው ከመመልከት ውጪ በቃላቸው ሆነ በጭብጨባድጋፍ ለመስጠት እንኳን አልሞከሩም። እንዲህ አይነቱ ከተለመደው ውጭ የሆነ የእብደትና የውንብድና ስራ ሲፈጸም ጣልቃ መግባትና ሁኔታዎችን መቆጣጠር የፀጥታ አስከባሪዎች ስራ ነው ።በሌሎች ሀገራትም በአንድም ይሁን በሌላ ምክንያት እንዲህ አይነት የውድመት ስራ ሲፈጸም ጣልቃ ገብቶ የሚቆጣጠር ዝግጁ የሆነ የአካባቢው ሀይል ነው። እንደ ችግሩ ስፋትም የመከላከያ ሰራዊት ሊጠራ ይችላል።የዛሬ 24 አመት አካባቢ በሎስ አንጀለስ የተቀጣጠለው ከፍተኛ አመጽ እና የውድመት ስራ ለመቆጣጠር 6000 የፌደራሉ የመከላከያ ሰራዊት መጠራት የነበረበት አጋጣሚ ጥሩ ምሳሌ ሊሆን ይችላል። በአማራ ክልል የተወሰኑ አካባቢዎች የተፈጠረው ችግር ከሚገባው በላይ እድሜ ሊያገኝ የቻለው በመንግስት የበዛ ትእግስት እና ተገቢ እርምጃ ለመውሰድ ከመዘግየት የተነሳ ነው እላለሁ። ከረጅም የሰላም እና የመረጋጋት አመታት ቡሀላ ድንገት የተከሰተው ይህ ሁኔታ በመንግስት በኩል መደናገር ቢፈጥርም ብዙ ሊያስገርም አይገባም ።ዋናው ከዚህ ትምህርት ወስዶ ለወደፊቱ ተዘጋጅቶ መጠበቁ ላይ ነው።ዛሬ ቀና ብለን የምናያቸው ያደጉ እና የተረጋጉ ሀገራትም በርካታ ግጭቶች እና ህገመንግስታዊ ፈተናዎችን እና ቀውሶችን አልፈው እንደሆነ እዚህ የደረሱት ማሰብ የግድ ይላል።በቅርቡ ያጋጠመን ችግር የመጀመርያ ችግራችንም አይደለም የመጨረሻም አይሆንም።ኢህአዴግ እና አብዛኛው የህብረተሰብ ክፍል ሊያስተውለው የሚገባ ትልቁ ቁምነገር ድምፁ የማይሰማ ብዙኃን (the silent majority)መኖሩን ነው።ድምፃቸው ከፍ ብሎ የሚሰማ ብዙሀኑን እንወክላለን የሚሉ በብዙሀኑ የተጠሉ ወገኖች ናቸው። ዛሬ የዜናውን ርእስ የያዙት እና የሚሰሙት ኢህአዴግ ህዝባዊ ወገንተኝነትን አላማው አድርጎ ሲነሳ ህዝባዊነት የጎደላቸው ወገኖች ጠላት አድርጎ ነው።በቀደሙት ሁለት መንግስታት ቀና ብለው ይሔዱ የነበሩ ፀረ ሰላም ሀይሎችን( ኦነግ፣ኦብነግና ሻዕብያን) ቋንጃቸው መትቶ ያሽመደመደ ድርጅት ነው።እነዚህ ወገኖቾ እና በሀይል የተገረሰሰው ስርአት ተጠቃሚዎች የነበሩ ክፍሎች አንድም ቀን ይህን ስርአት ከልቡ ወደውት እና ፈቅደው ተቀብለውት አያውቁም።ከወደቁበት ሆነው ቁስላቸው እየላሱ የዚህን መንግስት እና ስርአት ውድቀት ያልተመኙበት አንድም ግዜ የለም።ዛሬም ዘመኑ በፈጠረው እና አለም እየታመሰ ያለበትን የCYBER ጦርነት በመጠቀም በከፈቱት የማጥቃት ሙከራ ነፍስ የዘሩ የሚመስልበት ሁኔታ አለ።ይህ አለምን ስጋት ላይ የጣለ ጦርነት የካንሰርነት ባህርያት አሉት።በጊዜ ከተደረሰበት እና ተገቢውን ህክምና ካገኘ የመዳን፣ከእጅ ካመለጠ እና ከፍተኛ ደረጃ ከደረሰ መፍትሔ የሌለው እና ገዳይ ጦርነት ነው።ከሀገራችን ድንቅ አባባሎች አንዱ ” ጦር ከፈታው የፈታው”የሚለው ነው ። ወሬ የፈታው ግለሰብ እና ማህበረሰብ ብዙ መከራ ሊያገኘው ይችላል።በዚህ ችግር የቆሰለው እና የተጎዳውን መለየት አስቸጋሪ ነው የዚህ ችግር መፍትሔ ከሚገኝባቸው መንገድ አንዱ በሌላ ምሳሌያዊ አነጋገር ለመግለጽ ” እሾህን በሾህ”ነው።ኢህአዴግ ከሚታወቅባቸው ድክመቶች አንዱ ለፕሮፖጋንዳ ያለው ዝቅተኛ አመለካከት ነው። ” ስራ በቂ ነው” የሚል እምነት አለው።ስራ ግን በቂ አይደለም መሠራትም አለበት።በወሬ የተሰራውን እንዳልተሰራ ፣የሌለውን እንዳለ መልካሙን ክፉ አድርጎ ማሳየት ይቻላል። ስለዚህ፡የተከፈተብንን ስውር ጦርነት ለመመከት እና ለማምከን የሚቻለው በመጀመርያ ለችግሩ እውቅና መስጠት የመፍትሔው ግማሽ መልስ ተገኘ ማለት ነው።ቀጥሎም ምድር ላይ ከሚሰራው የጎደለውን የማረም እና መልካሙን የማጎልበት ስራ ጎን ለጎን በሚሄድ ሁኔታ በCYBER የመከላከል እና መልሶ የማጥቃት ስራውን ብቃት ባላቸው ሞያተኞች አጠናክሮ ማስከድ እጅግ አስፈላጊ ነው። በየትኛውም ሀገር ( እንኳን ዓይናን መግለጥ በጀመረች እና በስር ነቀል ለውጥ የሽግግር ሂደት ላይ በምትገኝ ሀገር )መቶ በመቶ ህዝብን ያረካ ስርአት የፈጠረ ፣ለመፍጠርም የሚሞክር የለም።

ሚስጥራዊ ወይም ቁልፍ ቃል “አብዛኛው” የሚለው ነው። በዚህ ረገድ ኢህአዴግ አብዛኛውን የህብረተሰብ ክፍል ተጠቃሚ ያደረገ እና ተስፋን ያስጨበጠ ስራ ለመስራቱ ቅንጣት ታህል መጠራጠር የለበትም።ከአቶ መለስ መማር ከምንችላቸው በርካታ ነገሮች አንዱ ፣በህዝብ አስተዋይነት፣ማለትም በአብዛኛው ህዝብ አስተዋይነት እና ቅን ፈራጅነት መታመንን ነው።ያ ሩቅ አሳቢ ነው፣በሄደበት የሚያየው እና የሚሰማው የጥቂቶች ከፍ ያለ የጥላቻ ድምጽ ትቶ ድምጹ የማይሰማውን ብዙሀን የማዳመጥ እና በእርሱ የመታመን ልዩ ችሎታ ነበረው፣ከብርታቱ ምንጮች አንዱም ይኸው ነበር ማለት ይቻላል።

በጋሻው ከበደ ለኢትዮጵያ ፕሮስፐረስ

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy