ተገቢ ትኩረት ያጣ አንገብጋቢ ጉዳይ
በኢህአዴግ ድርጅታዊ መግለጫም ይሁን ጠቅላይ ሚንስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙርያ ለጋዜጠኞች በሰጡት ማብራርያ ላይ ቦታ ያልተሰጠው ነገር ግን በሀገራችን የተወሰኑ አካባቢዎች ለተፈጠሩ አሳዛኝ ሁኔታ ወሳኝ ሚና ያለው ጉዳይ አለ፣ ይኸውም የተከፈተብን የማህበረሰብ ዜና ማሰራጫዎች እና አጠቃላይ የ CYBER ጦርነት ነው። በተለያየ አቅጣጫ የሚመጡና በታሪካዊ ጠላቶቻችን በጥሩ ሁኔታ የሚደግፉ የጥፋት ሀይሎች ያሰማሯቸው እነዚህ የዜና ማሰራጫዎች እንኳን የሒወት ተሞክሮ ያነሰውን ወጣት እድሜ የጠገበውንም የማሳት አቅም አላቸው። ይህ ችግር በእኛ ሀገር ብቻ የተወሰነ ሳይሆን አለምን በአጠቃላይ እየፈተነ ያለ የዘመናችን ትልቅ ችግር ነው።በምእራቡ አለም የሚኖሩ የተወሰኑ ወጣቶችን ከሞቀ ኑሮአቸው አንስቶ መያዣ መጨበጫው ወደ ጠፋባቸው የእልቂት ቀጠናዎች እየወሰደ ያለውም ይኸው ሰይጣናዊ መንገድ ነው።የዋሆቹን የምእራባውያን ወጣቶች በሚኖሩባቸው ሀገራት ላይም እልቂትና ሰቆቃን ለማድረስ የአጥፍቶ ጠፊነት ተግባር እንዲፈጽሙ ማድረግ ተችሏል። የጥፋት እና የውድመት አጀንዳ ያላቸው እና ዋና መቀመጫቸውን በውጭ ሀገራት ያደረጉ አንድ አንድ የሀገራችን ድርጅቶች እና ግለሰቦችም ከእነ ISIS ገጽ በመዋስ ወጣቱ ላይ ያተኮረ የጥላቻ እና የአመጽ ቅስቀሳዎችን አካሂደዋል። ከአመታት በፊት በተለያዩ ሀገራት ላይ የደረሱ የሞት አደጋዎች ልክ በእኛ ምድር ላይ እንደተፈጸሙ በማስመሰል ያሰራጭዋቸው የቅስቀሳ መልእክቶች ብዙዎችን አሳዝኗል፣አስቆጥቷልም።ለዚህ ትልቅ ምሳሌ የሚሆነው የአትሌት ፈይሳ ሌሊሳ ታሪክ ነው።አትሌቱ እንደዚህ አይነት ትልቅ ውሳኔ ለመወሰን ያበቃው የቅርብ ጉዳይ ማለትም ከቤተሰቡ መሀል የታሰረ ወይም የተገደለ ሰው መኖር አለበት በሚል ግምት ጋዜጠኞች ጥያቄውን ሲያቀርቡለት የታሰረም የተገደለም ዘመድ እንደሌለው እና በሩቅ ሆኖ በሰማው ብቻ በማዘን ይህንን ውሳኔ ለመወሰን መቻሉን ነበር የገለጸው ።ባለቤቱም ምን እንደተሰማት እና እንደዚህ እንደሚያደርግ ጠብቃ እንደሆነ ከሮይተርስ ለቀረበላት ጥያቄ ስትመልስ ” በኢንተርኔት ዜናዎች ላይ እያየ በጣም ይበሳጭ ስለነበረ ይህንን ማድረጉ ብዙም አላስገረመኝም።” ነበረ መልሷ ሰሙኑንም ነዋሪነታቸው በቶሮንቶ ካናዳ የሆኑ የቅድስት ማርያም ቤተክርስትያን አስተዳዳሪ በአንድ ቃለ ምልልስ ላይ ከጠቀሱት እጅግ ካዘኑባቸው ጉዳዮች መካከል ቦርሳ ይዛ መንገድ ላይ ሬሳዋ የወደቀችን ሴትጉዳይ ነበር፡ያቺ ሴት ከአመታት በፊት በአንድ የአፍሪካ ሀገር የሆነ ታሪክ እና በጊዜው ዜና ማሰራጫዎች ካወጡት ዜና ላይ የተወሰደ መሆኑን በማስረጃ ተገልጿል።ይህን የገጠመንን ችግር እድገታችን ያመጣብን ችግር በማለት የሚገለጽበት ሁኔታ ትልቅ እውነትነት አለው። ዛሬ በገጠሪቷ ኢትዮጵያ ውስጥ ቀላል የማይባል ቁጥር ያላቸው ወጣቶች የማህበራዊ ዜና ማሰራጫዎች ተጠቃሚ ናቸው።ማለትም አገልግሎቱን ለመጠቀም የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶችን ( ሞባይል ስልኮች እና የመሳሰሉትን) የመግዛት አቅም ተፈጥሯል ማለት ነው። ሰልፎቹ ወይም ሁከትና ግርግሮቹ የሚጠሩትም በማህበራዊ ዜና ማሰራጫዎች ነው ። ባለቤት የሌላቸው ሰልፎች/ እንቅስቃሴዎች የሚባሉትም ለዚህ ነው። ታዲያ በግልፅ የሚታይ ይህ ሁኔታ እያለታዲያ በግልፅ የሚታይ ይህ ሁኔታ እያለ